በአሜሪካ የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረት ደፋር አሸነፈች

አሜሪካ ሳንዲያጎ ግዛት በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረት ደፋር በሴቶች አንደኛ ሆና ስታሸንፍ በወንዶች ፈይሳ ለሊሳ ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡መሰረት በሳንዲያጎ የተደረገውን የማራቶን ውድድር ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ ነው፡፡

በውድድሩ ኬንያዊትዋ ጄን ኬቢ ሁለተኛ በመሆን መሰረትን ተከትላ ገብታለች፡፡

በወንዶች በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ቱቱስ ኢኩሪ አንደኛ በመሆን ሲያሸንፍ ፈይሳ ሌሊሳ ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡