13 ጄኔራሎችን ጨምሮ 41 ሺህ የአማራ ተወላጆች ከመከላከያ ሰራዊቱ በግፍ ተባረዋል።

ፀረ አማራው መከላከያ ሰራዊት

በማንነታቸው ከሰራዊቱ የተባረሩ አማራ #ጀኔራሎች
በአስር አመት ውስጥ ከ13 በላይ ጀኔራሎች፣ ከ45 በላይ ኮረኔሎች፣ ከ250 በላይ ሻለቆች ከ21 ሺህ በላይ ከመስመራዊ መኮንን እስከ ተራ ወታደር ብሔራቸው አማራ ስለሆኑ ተባርረዋል። ከዛ በፊት 20 ሺህ ወታደሮች ተባርረዋል። በአጠቃላይ ከ41 ሺህ በላይ የአማራ ተወላጆች ከሰራዊቱ ተባረዋል።
1) ብ/ ጀኔራል ተፈራ ማሞ
በተለያዩ የውጊያ ቦታዎች ላይ ሰራዊቱን መርቶ ተዋግቷል፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመሪነት ቦታ የሚያየው ሰው ነው። ጀኔራል ተፈራ የህወሃት የበላይነትን ከበረሃ ጀምሮ በመታገሉ “ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ፣ ፊውዳል” እየተባሉ ፍረጃ ሲሰጣቸው ከነበሩት መካከል ቀዳሚው ነው።
ከ1998 ጀምሮ አማሮች ከሰራዊቱ በማንነታቸው ሰበብ እየተፈለገ “በዲሲፕሊን” እየተባሉ ሲባረሩ ጀኔራል ተፈራ “በዲስፕሊን አይደለም” ብሎ ተከራክሯል። ከሰራዊቱ ለተባረሩት ድጋፍ ደብዳቤ በመፃፉ፣ በግምገማ ወቅት ስለህወሓት ጀኔራሎች ሙስና በመናገሩ ጥርስ ውስጥ ገብቷል።
የአማራ ተወላጅ የሆኑ የሰራዊት አባላት “ጀኔራል ተፈራ፣ ከጀኔራል ኃይሌ ጥላሁን ጋር ሆኖ መለስ ዜናዊን ለማስገደል እያሴረ ነው” ብለው በሀሰት እንዲመሰክሩበት ተገድደው በሀሰት አንመሰክርም በማለታቸው ከእስር ተርፎ ነበር። በመጨረሻም በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ክስ እድሜ ልክ ተፈርዶበት 9 አመት ታስሮ በቅርቡ ተፈትቷል። ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ከሙስና የፀዳ በመሆኑ በሰራዊት ዘንድ “ድሃው ጀኔራል” በመባል ይታወቃል።
2) ብ/ጀኔራል አሳምነው ፅጌ
~”ትምህርት ቤቱ ይፈርሳል እንጂ አማራ አይማርበትም” ጀኔራል ሳሞራ የኑስ
አሳምነው የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ ነበር። ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ የጀኔራልነት ማዕረግ አግኝቷል። የህወሃት የበላይነት በሰራዊቱ ውስጥ መኖሩን በመረጃ በመሞገት ሀረር በተደረገ 1993 መድረክ ላይ በመድረኩ ተሳታፊዎች ስምምነት እንዲደረስ አድርጓል።
ብ/ጀኔራል አሳምነው አሜሪካ ሀገር ለአንድ አመት ወታደራዊ ትምህርት ተምሯል። በ1997 ሀገራዊ ምርጫ ጊዜ “ቅንጅት ነው” ተብሎ ተፈርጆ ነበር።
አሳምነው መከላከያ ዩኒቨርሲቲን በብቃት መርቷል። ሆኖም ተቋሙን በሚመራበት ወቅት የህወሓት ሰዎች “አሳምነው አሜሪካ ሄዶ ያመጣው ነገር አለ” በሚል ያዋክቡት ነበር። አሳምነው ወደ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች (ወታደሮች) በፈተና እንዲገቡ በማድረጉ ጥርስ ውስጥ ገብቷል። በፈተናውም ብዙ የአማራ ልጆች በማለፋቸው የበለጠ አሳምነው ከህወሓት ሰዎች ጋር ተካረረ። እንዴት ብዙ አማራዎች ፈተናውን ሊያልፉ ቻሉ በሚል ሲጠየቅ አሳምነው ለእነ ጀኔራል ሳሞራ “ውጤቱን ካላመናችሁ ፈተናውን ራሳችሁ አውጥታችሁ ፈትኗቸው” ብሏቸዋል። እንዲያውም ጀኔራል ሳሞራ የኑስ “እንዲህማ አይሆንም፣ ትምህርት ቤቱ ይፈርሳል እንጂ አማራ አይማርበትም” እስከማለት ደርሶ ነበር።
ጉዳዩ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደርሶ በመጨረሻ በወታደራዊ ትምህርት ቤቱ የተነሳው መካረር አድጎ ጀኔራል አሳምነው እንዲታገድ ተደርጎ አለፎም እጂጉ የሚባል የህወሓት ሰው ሲተካ ዩኒቨርሲቲው ማስተማሩን ቀጠለ።
ጀኔራል አሳምነው ፅጌን ከሰራዊቱ ሲያባርሩት ማዕረጉን አንስተው ነበር። ጀኔራሉ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ክስ እድሜ ልክ ተፈርዶበት በቅርቡ ከ9 አመታት እስር በኋላ ተፈትቷል።
3) ጀኔራል ኃይሌ ጥላሁን
~”ከበደ እናገመቹ የት ሄዱ? ሀጎስና ገብረክርስቶስ በዙ!”
ኢህአፓ አሲምባ ላይ ጦር ሲመሰርት አባል ነበር። አየር ኃይል አዛዥ ሆኖም ሰርቷል። ባህርዳር ላይ በነበረውና ኃይሌ በመራው የሰራዊት ኮንፈረንስ የህወሓት የበላይነት አለ የሚለው ላይ መተማመን ላይ ተደርሷል። የህወሓት ሰራዊት አባላት የህወሓት የበላይነት አለ በመባሉ መድረክ ረግጠው ሲሄዱ “ለትግራይ ሕዝብ ቆምን ትላላችሁ እንጅ የትግይራ ህዝብ የብብት ቅማል ናችሁ” በማለቱ በህወሓት የሰራዊት አባላት ተጠምዷል። በህወሓት ትእዛዝ ኮንፈረንሱ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ለማዕረግ የታጩ ወታደሮችን ስም ዝርዝር አይቶ “ከበደ እናገመቹ የት ሄዱ? ሀጎስና ገብረክርስቶስ በዙ!” በማለቱ በህወሓት የጦር ሰራዊት አባላት ጋር የከረረ ጠብ ውስጥ ገብቷል። የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሁለት የሰራዊቱ አባላት ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጋር በመሆን አቶ መለስ ዜናዊን ለማስገደል ሙከራ አድርጓል ብለው በሀሰት እንዲመሰክሩበት ቢገደዱም በሀሰት አንመሰክርም ብለው ሳይመሰክሩበት ቀርተዋል።
ጀኔራል ኃይሌ””የኢህአፓ ርዝራዥ” የሚል ስም ተሰጥቶት በኋላ ቤቱን ቀምተው፣ ጥቅማጥቅሙን ነጠቁት። ጦር ሀይሎች ትሰራ ከነበረችው ሀኪም ባለቤቱ ጋር በተመሳሳይ ቀን ከስራ አባረውታል። ሰብዕናውን ከገደሉ በኋላ ሰላም አስከባሪ ልከውት መሞቱ ተሰምቷል።
4) ጀኔራል ተመስገን አበበ
የተሻለ ትምህርት አላቸው ከሚባሉት ጀኔራሎች መካከል አንዱ ነው። በእድሜም ወጣት ጀኔራል ሲሆን ወታደራዊ ኢንዶክትርኔሽን ውስጥ ሰርቷል። የምዕራብ እዝ አስተዳደር ኃላፊ ነበር። ቅንጅት ተብሎ ከተባረሩት መካከል ነው። ጀኔራል አብርሃ ወ/ማርያም (ኳርተር) ግምገማ ላይ “አንተ ቅንጅት ነህ” ብሎ በግልፅ ነግሮታል።

5) ጀኔራል ባዬ ወንድአፍራሽ

~ስዬና ፃድቃን ጨምሮ ሰራዊቱን ወታደራዊ ሳይንስ ያስተማረ
በደርግ ዘመን ሩሲያ አምስት አመት ወታደራዊ ሳይንስ ተምሯል። እነ ስዬ እና ፃድቃንን ጨምሮ ጦሩን ካርታ ገለፃ ያስተማረ ነው። የምስራቅ አፍሪካ ብርጌድ አዛዥ ነበር። የመከላከያ ስታፍ ስልጠና ክፍል ነበር። የወታደራዊ ሳይንስ ኤክስፐርት ነው። በማንነቱ ምክንያት ከሰራዊቱ ተባርሯል።
6) ጀኔራል ምስጋናው አለሙ

– ህክምና ተነፈጎ ከሰራዊቱ የተገፋው ጄኔራል!
ጀኔራል ምስጋናው ከ1974 ጀምሮ የታገለ፣ የክፍለ ጦር አዛዥ ነበር። ጄኔራል ምስጋናው አለሙ አሁን ላይ በቂ ህክምና አጥቶ ህመም ላይ ይገኛል። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ባድሜ ግንባር ተሰልፎ ተዋግቷል።
ጀኔራል ምስጋናው አለሙ በማንነቱ ምክንያት ከሰራዊቱ ተገፍቶ እንዲወጣ ተደርጓል።

7) ጀኔራል ወንዶሰን ተካ
ከሰራዊቱ ከተባረሩት የአማራ ተወላጅ ጀኔራሎች መካከል ወጣቱ ነው። በምስራቅ እዝ ስር የምትገኘው 32ኛ ክፍለ ጦር መሪ ነበር። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ቡሬ ግንባር 39ኛ ክ/ጦር አዋግቶ ጥሩ ድል ያስመዘገበ፣ ሞቃድሾ ጦር የመራ ጀኔራል ነው። በመፈንቅለ መንግስት ተጠርጥረው ከታሰሩት ከእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጋር ግንኙነት አለህ ተብሎ ከሰራዊቱ ተባርሯል።

8 ) ጀኔራል ስዩም ሀጎስ

“አማራ ነኝ!” ጀኔራል ስዩም
ጀኔራል ስዩም የምዕራብ እዝ አዛዥ ሆኖ ሰርቷል። መጀመርያ የህወሓት ታጋይ የነበር ሲሆን “አማራ ነኝ” ብሎ ኢህዴንን ተቀላቀለ። ስዩም ትውልዱ ኮረም ሲሆን የህወሓት ሰዎች አማራ ነኝ ስለሚል ቤተሰቦቹ ድረስ ሄደው አነጋግረዋል። እነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ ግንኙነት አለህ ተብሎ ተባርሯል።

9) ሌ/ጀኔራል አበባው ታደሰ

ሌ/ጀኔራል አበበው ታደሰ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ነበር። በወታደራዊ አሰራር በማዕረጉ ከጀኔራል ሳሞራ ቀጥሎ “ሲኒየር” በመሆኑ ቀጣዩ ኢታማዦር ሹም ሊሆን ይችል ነበር። ጀኔራል አበባው ጀኔራልነት ማዕረግን ሲያገኝ በእድሜ ትንሹ ጀኔራል ነበር። አበባው በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ባድመ ግንባር 108ኛ ጦርነት እየመራ ጀብድ ፈፅሟል።
ሌ/ጀኔራል አበባው በ2006 ዓም ከመከላከያ ሰራዊት ተባርሯል። አበባው በህዝብ ላይ የሚፈፀመውን በደል በግልፅ የሚቃወምና የህወሓት የበላይነት ላይ ጥያቄ ባያነሳም ማንነቱ ከመገለል አላዳነውም።

10) ጀኔራል አለሙ አየለ:_
የመከላከያ ስታፍ ሆኖ ሰርቷል። እንደ ሌሎቹ የአማራ ተወላጅ ጀኔራሎች በህወሓት የበላይነት ላይ በግልፅ ተቃውሞ ባያነሳም በማንነቱ ምክንያት ከሰራዊቱ ውጭ ተደርጓል።

11) ጀኔራል አበራ ድኩል:_
76 ኢህዴንን የተቀላቀለ፣ የሰሜን እዝ አስተዳደር የነበረ። በማንነቱ ምክንያት ከጦሩ እንዲሰናበት ተደርጓል።
12) ጀኔራል አከለ አሳዬ ጀኔራል:_
ኢትዮ ኤርትራ ጊዜ ኮር አስተዳደር፣ በኋላም ብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ኃላፊ ነበር፣ ባድሜ ግንባር ተሳትፏል። ገና ወጣት ጀኔራል ነው። በማንነቱ ምክንያት ከሰራዊቱ ተባርሯል።

(ጀኔራሎቹ ከ1997 ዓም በኋላ ከቅንጅት ጋር፣ እንዲሁም ከ2001 ዓም በኋላ ከእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጋር ግንኙነት አላችሁ እየተባሉ ከጦሩ ተባርረዋል)

በማንነታቸው ምክንያት ከሰራዊቱ የተባረሩ 45 የአማራ ተወላጅ ኮሎኔሎች

1) ኮ/ል ፋንታሁን ሙሃባ (9 አመት የታሰረ)
2) ሽኩር አህመድ (ቅንጅት ተብሎ ታስሮ የተባረረ)
3)ኮ/ል ግርማ ገሰሰ (ውጭ ወጥቶ የቀረ)
4) ኮ/ል ሙሉአለም መሸሻ
5)ኮ/ል አዳነ ሽመልስ
6)ኮ/ል ባዬ አበበ
7)ኮ/ል ጥጋቡ ታመነ
8/ ኮ/ል አበበ ላቅያለው
9 ) ኮ/ል ኢትዮጵያ ገ/መድህን
10)ኮ/ል ሸጋው ጓሌ
11) ኮ/ል አድና በላይ
12) ኮ/ል ፍቃዱ ማማዬ
13) ኮ/ል ስንታየሁ
14) ኮ/ል አስቻለው
15) ኮ/ል መኮንን ሰኢድ
16) ኮ/ል ጥሩነህ ማሞ
17) ኮ/ል ጌታቸው ተሰማ
18) ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ (ጎንደር ላይ አፈና የተደረገበት)
19) ኮ/ል አበበ አስራት(ቅንጅት ተብለው 12 አመት የታሰሩ)
20) ኮ/ል ጎሳዬ ቦጋለ (ቅንጅት ተብለው 12 አመት የታሰሩ)
21) ኮ/ል ከበደ
22) ሌ/ኮ ጌታቸው ብርሌ (9 አመት የታሰረ)
23) ሌ/ኮ አበረ አሰፋ (9 አመት የታሰረ)
24) ሌ/ኮ አለሙ ጌትነት (9 አመት የታሰረ)
25) ሌ/ኮ ደምሰው አንተነህ (9 አመት የታሰረ)
26) ሌ/ኮ ሰለሞን አሻግሬ (9 አመት የታሰረ)
27) ሌ/ኮ አስፋው እጅጉ
28) ሌ/ኮ እንድሪስ ሰኢድ
29/ ሌ/ኮ አባይ ካሴ (ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ)
30) ሌ/ኮ አጥሌ ደምሴ (ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ)
31) ሌ/ኮ አዛናው አለሙ (ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ)
32) ሌ/ኮ የሽዋስ አጥናፉ (ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ)
33) ሌ/ኮ ያለው ስዩም
34) ሌ/ኮ ዘውዱ አሊ
35) ሌ/ኮ አበበ ተስፋዬ
36) ሌ/ኮ ምስራቅ ጌታቸው
37)ሌ/ኮ ዘየደ ለገሰ
38) ሌ/ኮ ደሳለኝ አንዳርጌ
39) ሌ/ኮ ደሴ ዘለቀ
40) ሌ/ኮ ስለሽ ዳኘ
41) ሌ/ኮ አለበል አማረ (1አመት ታስሮ የተባረረ)
42) ሌ/ኮ እሱባለው አያሌው
43) ሌ/ኮ አባይ
44) ሌ/ኮ መኮንን
45) ሌ/ኮ ጌትነት (7 አመት የታሰረ)

በማንነታቸው ምክንያት ከሰራዊቱ ከተባረሩ የአማራ ተወላጅ ሻለቆች መካከል:_

1)ሻለቃ መሰከረ ካሳ (9አመት የታሰረ)
2) ሻለቃ መኮንን ወርቁ (9 አመት የታሰረ)
3) ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ (9አመት የታሰረ)
4) ሻለቃ አደፍርስ አሳምነው (7አመት የታሰረ)
5)ሻለቃ አዱኛ አለማየሁ (7 አመት የታሰረ)
6) ሻለቃ ተስፋዬ እንዳለ
7) ሻለቃ ሲሳይ ቸኮል (ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ)
8/ሻለቃ መኮንን ብርቁ
9) ሻለቃ የሺ አበራ
10) ሻለቃ ያለው ጀንበሬ
11) ሻለቃ ጓንቼ
12) ሻለቃ ፀጋ
13) ሻለቃ አምሃ
14) ሻለቃ ነይኑ ሽፈራው
15) ሻለቃ እያሱ ይትባረክ ይገኙበታል። በአጠቃላይ ከ250 በላይ የአማራ ተወላጅ ሻለቆች በማንነታቸው ምክንያት ከሰራዊቱ ተባርረዋል!

በ2008 ዓም አማራ ክልል ነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት የተባረሩት የሰራዊት አባላት

በ2008 ዓም በአማራ ክልል በነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለይ በባህርዳር እና ጎንደር “ህዝብ ጥያቄ ስላነሳ መልሱ ግድያ መሆን የለበትም” ብለው የተቃወሙ የሰራዊት አባላት እና አመራሮች ተባርረዋል። ኃይለማርያም ደሳለኝ በሕዝብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ የተቃወሙት አብዛኛዎቹ ከታሰሩ በኋላ ተባርረዋል። ጅጅጋ ላይ ሳሞራ እና በረከት በመሩት ስብሰባ በእነዚህ የሰራዊት አባላት ላይ የተደረገው የጅምላ ማባረር የዘር ማፅዳት ነው ሲሉ የተናገሩ ጀኔራሎችም ነበሩ። ከዚህ በኋላ የተወሰኑት በቦርድ እንዲተዳደሩ ተደርገዋል። ገና በለጋ እድሜያቸው ከሰራዊቱ አባርረው በቦርድ ይተዳደሩ ካሏቸው በተጨማሪ ብዙ የአማራ ተወላጅ የሰራዊት አባላት በ2008 ሕዝባዊ ንቅናቄ ሰበብ ተባርረዋል።

በማንነታቸው ምክንያት ስቃይ የደረሰባቸውን የአማራ ተወላጅ የሰራዊት አባላት

1) ኮ/ል አበረ አሰፋን ለምስራቅ ጦር ስራ ላይ እያለ አስረው ጥፍሩን ነቅለውታል
2) ይበልጣል ብርሃኑን በምርመራ ወቅት ብልቱ ላይ ውሃ የሞላ “ሀይላንድ” አንጠልጥለውበታል
3) ጌቱ ወርቁ 19 ሰዓት እጁን ጣራ ላይ ታስሯል
4) ተመስገን ባይለየኝ ለረዥም ጊዜ በካቴና በመታሰሩ እጁ ተመልጧል።
4) ኮ/ል ደምሰው አንተነህ ሊያመልጥ ነበር ተብሎ ከተያዘ በኋላ ሁለት እግርና ሁለት እጁን በጥይት መትተውታል።

የአማራ ተወላጆች ከሰራዊቱ የሚባረሩበት ሰበብ
1) ከ1997 ዓም እስከ 2000 ዓም ቅንጅት ናችሁ ተብለው ተፈርጀው
2) ከ2000 ዓም በኋላ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ እየተባሉ
3) አማራ በመሆናቸው ወደ ከፍተኛ አመራር መውጣት ስለሌለባቸው፣ በአማራነት ተደራጅተዋል በሚል
4) ውስጣዊ ትግል ስለሚያደርጉ፣ እውነታውን በመናገራቸው
5) የህወሓትን ከፋፍለህ ግዛ በመቃወማቸው እና ስለ ሀገራቸው ባላቸው ቀና አመለካከት
6) የማደግ ተስፋቸውን ለመቅጨትና በአመራር የህወሓት ተራ ወታደር ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ በተለይም ከ1997 በኋላ የህወሓት ሰራዊት ለመካከለኛ አመራር ክፍተት በመፈጠሩ የህወሓትን ወታደራዊ የበላይነት አስጠብቆ ለመቀጠል ከዩኒቨርሲቲና ካሉት ወታደሮች ወደ መካከለኛ አመራርነት ለማብቃት ለአመራርነት የሚመጥኑት የአማራ ተወላጆች በሰበብ ተባርረዋል፣ ትምህርት ተከልክለዋል።

የሚያጥላሉበት መንገድ

1) ትምክተኛ እና ነፍጠኛ ብሎ በመፈረጅ
2) የድሮ መንግስታትን ትናፍቃላችሁ በሚል ውንጀላ
3) እውነታውን ሲያጋልጡ ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደሉም ብሎ በማጥላላት
4) አማራውን የስርዓቱ ስጋት ነው ብሎ በግልፅ በመፈረጅ

በፀረ አማራነታቸው በሰራዊቱ እንዲቆዩ የተደረጉ አማራ ጀኔራሎች

1) ጀኔራል አደም መሃመድ:_ አየር ኃይል አዛዥ ነው። አማራው ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ዝም ከማለቱ ባሻገር፣ አንተ ነፍጠኛ እያለ አማሮችን የሚያወግዝ ሰው ነው። በ2010 ዓም የተደረገውን የሰሜን ወሎ ተቃውሞን ለመቀልበስ በሄሊኮፍተር የታገዘ ጥቃት እንዲደረግ የእሱ አስተዋፅኦ አለበት። የህወሓትን የበላይነት ለማስጠበቅ የትኛውንም መስዋትነት የሚከፍል ሰው ነው።
2) ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም:_ መረጃ ክፍል ነው። ወደሰራዊቱ የገባው 84 ሲሆን የረባ የውጊያ ታሪክ ሳይኖረው ጀኔራልነት ማዕረግ ሰጥተውታል። አማራ ጠል የሆነው የአብርሃ ወልደማርያም (ኳርተር) መረጃ ሲሆን የአማራ ጀኔራሎች ከሰራዊቱ እንዲገፉ በማድረግ እጁ አለበት።

ሻለቃ ምስጋናው እና ሻለቃ አዱኛ የተባሉ በማንነታቸው የታሰሩት የአማራ ተወላጆችን የመረመረ እሱ ሲሆን ጀኔራል ኃይሌ ጥላሁን እና ጀኔራል ተፈራ ማሞ መለስን ለማስገደል እየሰሩ ነው ብላችሁ መስክርባቸው ብሎ የሀሰት ምስክር አድርጎ ሊያቀርብባቸው ነበር።

3) ሜ/ጀኔራል መሰለ በለጠ:_ ከዚህ በፊት በማንነቱ ምክንያት በደል ደርሶበታል። ማዕረጉን ተቀንሷል። ይህን በማንነቱ የሚደርስበትን ጥቃት ለመከላከል የመረጠው አድርባይ መሆንን ነው። ከህወሃት የሰራዊት አባላት ጋር በትግርኛ ነው የሚያወራው። ኮ/ል ደምሰው አንተነህን ከስራ ያባረረው ኳርተር ነው። ኳርተር ሰላምታ ሰጥቶት ሲያልፍ፣ ጀኔራል በለጠ ፊቱን ዞሮበት ነው የሄደው። አንድ ሰው በሕወሓት ጥርስ ውስጥ ከገባ ከህወሓት ሰዎች በላይ የጠላ በመምሰል እነሱን ለማስደሰት ይጥራል።
4) ሜ/ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ:_መጀመሪያ የታገለው ከህወሓት ጋር ነው። የህወሓት አምላኪ ነው። ከህወሓት ሰዎች ጋር በአማርኛ አውርቶ የማያውቅ አድርባይ ነው። የሰራዊት አባላት በአማራነታቸው እየተሳሳቡ ነው ብሎ ለህወሓት አመራሮች ወሬ ያቀብላል።

አብርሃ ወ/ማርያም፣ ፀረ አማራው የህወሓት ጀኔራል

~”አማራዎች ትምህርት ተምረው ሲመለሱ ለስርዓቱ ጠላት ይሆናሉ”
ፀረ አማራ ከሆኑት የህወሓት ጀኔራሎች መካከል ቀዳሚው ጀኔራል አብርሃ ወ/ማርያም (ኳርተር) ነው። ይህ ጀኔራል በአማራ የሰራዊት አባላት ላይ ያለውን ጥላቻ በግልፅ የሚናገር፣ ለማዕረግ የተመለመሉ የሰራዊት አባላትን ዝርዝር አይቶ “አማራ መጣብን” እያለ የሚናገር፣ ባህርዳርና ሀረር በተደረጉ ግምገማዎች በርካታ የአማራ ተወላጆችን ከሰራዊቱ ያባረረ ጀኔራል ነው።
ኳርተር በአኙዋክ፣ ሀዋሳና ሶማሊ ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ መርቷል የሚባል ሰው ነው። ሰራዊቱ እጃቸው በሙስና ተጨማልቋል ብሎ ከሚገመግማቸው ጀኔራሎች መካከል አንዱ ነው።
አማራ የሆኑ የሰራዊት አባላት የውጭ ትምህርት እድል ሲያገኙ “አማራዎች ትምህርት ተምረው ሲመለሱ ለስርዓቱ ጠላት ይሆናሉ” እያለ ፀረ አማራነቱን በግልፅ የሚናገር ነው።

አማራ በመሆናቸው ከሜቴክ ከተባረሩት መካከል በጥቂቱ
1. ሻለቃ አዱኛ ወርቄ በመከላከያ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የHO ተማሪ የነበረ አማራ በመሆኑ ብቻ ሊመረቅ 1 ሰሚስተር ሲቀረው የተባረረ
2. ሻምበል አለነ አይቸው (ኢንጂነር) በሜቴክ የደጀን አቪዬሽን ማርኬቲንግ ማናጀር የነበረ
3. ሻምበል ቀለሙ (ኢንጂነር)በሜቴክ የደጀን አቪዬሽን ፓወር ፕላንት ኃላፊ የነበረ
4. መ/አለቃ ያዕቆብ ባለህ (ኢንጂነር) በሜቴክ የደጀን አቪዬሽን ሮተሪ ዊንግ ግሩፕ ሊደር የነበረ
5. ወታደር (ኢንጂነር) ተስፋ ሁነኛው በሜቴክ ደጀን አቪዬሽን ፋይበር ግላስ ቴክኖሎጂ ኃላፊ የነበረ ህክምና ላይ እያለ ህክምናውን ሳያጠናቅቅ የተሰናበተ (የህክምና ስህተት የተፈፀመበት የግራ ኩላሊቱን ታሞ የቀኙን ነበር የቀደዱት)