የአዲሱን ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ በማፅደቅ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባውን አጠናቀቀ

የኢህአዴግ ምክር ቤት የአዲሱን ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ በማፅደቅ ስብሰባውን አጠናቀቀ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት የአዲሱን ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቋል፡፡

በሁለተኛ ቀን ውሎው ዛሬ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት ከመከረ በኋላ የተገኙት አባላት በሙሉ ድምጽ ማፅደቃቸው ነው የተነገረው፡፡

በመጀመሪያ ቀን ውሎው ምክር ቤቱ የፓርቲውን ውህደትና ፓርቲው ወደ ፊት የሚመራበት ፕሮግራም ላይ በመምከር አጽድቋል፡፡