ሐዋሳ ድምፅ የሚሰጠዉ ሕዝብ ከምንም በላይ ሰላሙ እንዳይታጎል አበክሮ እየተማፀነ ነዉ።

ለረጅም ዓመታት ሲያወዛግብ አንዳዴም ደም አፋሳሽ ግጭት ሲቀሰቅስ የቆየዉ የሲዳም ዞን የአስተዳደርነት ሥልጣን ነገ ሲወሰን የሐዋሳም ዕጣ ፈንታ አብሮ ይወሰናል

DW : እስካሁን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መስተዳድርን በርዕሠ-ከተማነት የምታገለግለዉ ሐዋሳ ወደፊት በዚሕ አገልግሎቷ መቀጠል አለመቀጠሏ ሊወሰን የዛሬ ሌሊት ብቻ ነዉ የቀረዉ።ለረጅም ዓመታት ሲያወዛግብ አንዳዴም ደም አፋሳሽ ግጭት ሲቀሰቅስ የቆየዉ የሲዳም ዞን የአስተዳደርነት ሥልጣን ነገ ሲወሰን የሐዋሳም ዕጣ ፈንታ አብሮ ይወሰናል።እስከዚያዉ ግን የነገዉን ሕዝበ ዉሳኔ ለማስተናገድ ሐዋሶች ሰሞኑን «ጠብ እርግፍ» ሲሉ ነዉ የሰነበቱት።በተለይ ሕዝበ ዉሳኔዉን ለመከታተል ወደ ሐዋሳ የተጓዘዉ የአዲስ አበባ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ እንደሚለዉ ድምፅ የሚሰጠዉ ሕዝብ ከምንም በላይ ሰላሙ እንዳይታጎል አበክሮ እየተማፀነ ነዉ።