በሕዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳንን የሚጎዳ ደርጊት እንዳትፈጽም የአረብ ፓርላማ አሳሰበ

Arab Parliament sends message to Ethiopian leaders affirming its solidarity with Egypt on GERD dispute

The resolution emphasized the parliament’s solidarity with Egypt and Sudan in protecting their water security

The president of the Arab Parliament Mishaal bin Fahm Al-Salami (Photo: Al Ahram)

የአረብ ፓርላማ ጠንካራ ማሳሰቢያ ለኢትዮጵያ መሪዎች መላኩ ተሰማ
የአረብ ፓርላማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የአቋም መግለጫ መላኩን ይፋ አድርጓል፡፡የአረብ ፖርላማ ትላንት ግብጽና ሱዳን የአባይ ዉሀ ላይ ያላቸውን መብቶች እንዲከበር ከሁለቱ አገራት ጎን እንደሚቆም ለኢትዮጵያ መሪዎች አቋሙን ማስታወቁን አል አህራም ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የአረብ ፓርላማ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 30 ቀን ፣ 2019 የአባል አገራት ባካሄዱት ስብሰባ የደረሱበትን የአቋም መግለጫ ለኢትዮጵያ መሪዎች መላካቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡በዚሁ መልክታቸውም በሶስቱ ሀገራት የተጀመረው ድርደር ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቅ ካልቻለ ፤ የአረብ ፓርላማ አባል አገራት ከግብጽና ሱዳን ጎን እንደሚቆሙ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የአረብ ፓርላማ ኘሬዚዳንት ማሻል ቢን ፋሀም አል ሳሊም በቲውተር ገፃቸው እንደገለፁት፤ ፓርላማው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው መልእክት ለግብጽና ለሱዳን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይጠቅሳል፡፤ ፡፡በመግለጫቸው ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳንን የሚጎዳ ደርጊት እንዳትፈጽም አሳስበዋል፡፡

http://english.ahram.org.eg/NewsContentP/1/356090/Egypt/Arab-Parliament-sends-message-to-Ethiopian-leaders.aspx?fbclid=IwAR3DUg7EfrFK_immk7BFil37rAJMklISRmQh0MU-nU5kvjYLtlUCVMkOY5s