የኢሕአዴግ ዉሕደት ዕቅዱና መዘዙ

DW : የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ (ኢሕአዴግ) ወደ ዉሑድ ፓርቲነት ቢለወጥ፣ ከፓርቲ መዋቅራዊ ለዉጥ ባለፍ በኢትዮጵያ ፌደራዊ ሥርዓት ላይ ብዙም ለዉጥ እንደማያስከትል ሁለት አንጋፋ ፖለቲከኞች አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እስካሁን «አጋር» የሚላቸዉን ፓርቲዎች ጨምሮ በቅርቡ ከግንባርነት ወደ ዉሕድ ፓርቲነት እንደሚቀየር በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የኢሕአዴግ ዋና መስራች ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የዉሕደቱን ሐሳብ እንደማይቀበለዉ አስታዉቋል። የሕወሓት መስራች ዶክተር አረጋዊ በርሔና ከሕወሓት ጋር ኢሕአዴግን የመሰረተዉ የቀድሞዉ ኢሕዴን መስራች አቶ ያሬድ ጥበቡ እንደሚሉት የሕወሓት ዉሕደቱን መቃወሙ ተገቢ አይደለም።ነጋሽ መሐመድ ሁለቱን ፖለቲከኞች አነጋግሯል።

የያኔዎቹ አማፂ ቡድናት ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ዛሬ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)የሚባለዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን)በ1981 የመሠረቱት ግንባር፣ አዳዲሶቹ መሪዎቹ እንደሚሉት፣ በነበር የሚዘከርበት ጊዜ ሩቅ አይደም።ግንባሩ ከሁለት፣ ወደ አራት ፓርቲዎች አስተናባሪነት፣ ከሽምቅ ተዋጊነት ወደ ገዢ መንግሥትነት የተለወጠበት ጉዞ እነሆ ከፍፃሜዉ መጀመሪያ ላይ ደርሷል።

ሒደቱ በርግጥ ዕድገት

Äthiopien Yared Tibebu (Government Communication Affairs Office/Kewot Woreda) ብቻ አይደለም።ዉጤትን ከዉድቀት፣ ትብብርን-ከክፍፍል፣ ፍቅርን ከጠብ፣ ሕዝባዊ ድጋፍን ከተቃዉሞ የቀየጠ ጭምር እንጂ።31 ዓመት።የ31 ዓመቱን የድል-ሽንፈት ቅይጥ ታሪክ-ለነበር ዝክር ከማሕደር ይዶላል የተባለዉ ዉሕደት የእስካሁኑን አወቃቀር መቀያየሩ የማይቀር ነዉ።

ብዙ ጊዜ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ሌላ ጊዜ ልማታዊ መንግስት፣ ሌላ ጊዜ አዉራ ፓርቲ የሚባሉትን  መርሆችም አራግፎ ምናልባት «መደመር» በሚለዉ በአዲሱ የግንባሩ መሪ መርሕ ይለዉጣቸዉል ወይም ይዉጣቸዋል የሚሉም አሉ።

ይሁን እንጂ ግንባሩ በሕገ-መንግስት በኩል ለኢትዮጵያ የበየነዉ ወይም የበየነባት የብሔር ፌደራሊዝምና ተያያዥ መርሆች፣ የሕወሓት መስራችና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሔ እንደሚሉት፣ መቀየራቸዉ አጠራጣሪ ነዉ።

በ31 ዓመቱ ጉዞ ከኢዮጵያነት ወደ ዐማራነት «የቀነጨረዉ» የቀድሞዉ የኢሕዴን መስራች እና የፖለቲካ ተንታኝ ያሬድ ጥበቡ ዉሕደቱ የፓሪቲ እንጂ ሕገ-መንግስትን የሚተካ አይደለም ይላሉ።

ኢሕአዴግ እንደተባለዉ ከተዋሐደ እስካሁን አጋር የሚላቸዉ የሶማሌ፣የሐረሪ፣የአፋር፣ የጋምቤላና የበኒ-ሻንጉል ገዢ የፖለቲካ ማሕበራት ከነባሮቹ

Äthiopien Tigrean Alliance for National Democracy | Aregawi Berhe & Asgede Gebreselassie (DW/S. Muchie) ፓርቲዎች ጋር ይቀየጣሉ። እኩል ድምፅ ይኖራቸዋልም።የዉሕደቱ ሐሳብ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዉሐደቱን ሲያቀነቅን ከነበረዉ ከትግራይ ገዢ ፓርቲ፣ ከኢሕአዴግ መስራችና ከእስከ ቅርብ ጊዜዉ የግንባሩ አድርጊ ፈጣሪ ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሕወሐት ተቃዉሞ የገጠመዉ መሆኑ ነዉ ግራዉ።

እንደሚባለዉ ኢሕአዴግ ወደ ዉሁድ ፓርቲነት እንዲለወጥ ከ1996 ጀምሮ በመርሕ ደረጃ ተቀብሎት ሲገፋ የነበረዉ ሕወሓት የጀመረዉ ከግብ ሊደርስ ሲል አሁን የወለፊንድ መቃወሙ ለብዙዎች  አስገራሚ፣ ለሌሎች እንቆቅልሽ ነዉ።አቶ ያሬድ እንደሚሉት ሕወሓት ዉሕደቱን በመቃወም ሕጋዊ-እዉቅና የሌለዉ አስተዳደር እስከማቆም እድረሳለሁ ማለቱ ለማንም አይበጅም።

ዶክተር አረጋዊ

Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF) በርሔ ግን የተቃዉሞዉ ምክንያት የሕወሓት መሪዎች ከስልጣን ሌላ ሌላ ነገር ስለማያስቡ ነዉ ባይ ናቸዉ።በዉሕደቱ ሒደት፣ አቶ ያሬድ እንዳሉት ከዚሕ ቀደም እንደተለመደዉ የፓርቲ አሰራር በአባላት ዘንድ ተደጋጋሚ ወይይት፣ ሰፊ ክርክርና ትችት አለመደረጉ፣ የሩቁም የቅርቡም ታዛቢ የድጋፍ ተቃዉሞዉን  ትክክለኛ ምክንያት፣ ጥልቀት-ምጥቀትን በቅጡ እንዳይለካ ግርዶሽ ሆኖበታል።