ምስራቅ ሀረርጌ ቤተ ክርስቲያን እንዲቃጠል ተደርጓል- ምእመናን ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል

በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ከሚገኙ እና ኅዳር 2 እና 3 ቀን 2012 ዓ.ም ጥቃት ከደርባቸው አብያተ ክርስቲያን መካከል በአክራሪዎች የተቃጠሉት ጥንታውያኑ ገልዲድ ማርያም እና ዋቅጅራ ደብረ ገነት መዳኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን::
Photo ምንጭ:- ማህበረ ቅዱሳን

ምስራቅ ሀረርጌ ስላሉ ቤተ ክርስቲያኖች መረጃ! Elias Meseret

በዚህ ዙርያ የቻልኩትን ያህል መረጃ ለማግኘት ስሞክር ነበር። እስካሁን ያገኘሁት መረጃ ይህ ነው፣ ተጨማሪ ካገኘሁ እመለስበታለሁ:

የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ፀሀፊ ሊቀ ኀሩያን ፍስሀፅዮን አደመ ዛሬ ለቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት፣ ለብፁእ ወቅዱስ ልዩ ፅ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት እንዲሁም ለጠ/ሚር ፅ/ቤት የፃፉትን ደብዳቤ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቢሮ ዛሬ ከሰአት በመገኘት ለማየት ችዬ ነበር። ደብዳቤው ይህን ይገልፃል:

1. ህዳር 3, 2012 በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የዋቅጅራ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን እንዲቃጠል ተደርጓል

2. እንዲሁ የገልዲድ ደ/ፅ/ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያንም እንዲቃጠል ሆኗል

3. ቀርሳ ከተማ በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች በሆኑ ምእመናን ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል፣ 12 መኖርያ ቤቶችም ወድመዋል

4. በወተር ደ/ም/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን እና የምእመናን ቤት ላይ በድንጋይ ድብደባ ደርሷል

በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ከሚገኙ እና ኅዳር 2 እና 3 ቀን 2012 ዓ.ም ጥቃት ከደርባቸው አብያተ ክርስቲያን መካከል በአክራሪዎች የተቃጠሉት ጥንታውያኑ ገልዲድ ማርያም እና ዋቅጅራ ደብረ ገነት መዳኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን::
Photo ምንጭ:- ማህበረ ቅዱሳን

ከዚህ በመቀጠል ያናገርኳቸው የቀርሳ ወረዳ የፖለቲካ አደረጃጀት ሀላፊ የሆኑትን አቶ ሳላሀዲን ዩሱፍን ነበር። እርሳቸው ሲመልሱም:

“እኛ ጋር ያሉ ቤተ ክርስቲያኖችን ሙስሊሙም፣ ክርስቲያኑም በአንድነት የሰራው ነው። በቀርሳ ወረዳ ምንም የተቃጠለ ቤተ ክርስቲያን የለም። አንድም እንዲህ አይነት ነገር የለም፣ መስጊድም ላይ እንዲሁ የደረሰ ጥቃት የለም። የሆነው ነገር ትናንት ድሬዳዋ ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋር ይያያዛል። የእኛ አርሶ አደሮች ጫት ለመሸጥ ድሬዳዋ ይሄዳሉ። እዛ ሲደርሱ ግን ድብደባ ደረሰባቸው፣ ገንዘባቸውም ተዘረፈ። እንደምንም ብለው ወደ ወረዳቸው ሲመለሱ ህብረተሰቡ በድንጋጤ ውስጥ ነበር፣ በዛ መሀል አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር እንጂ ወረዳው ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ላይ ምንም ጥቃት አልደረሰም።”

ሰላም ለሀገራችን!