የአሃዱ ሬዲዮ ጋዜጠኛ በአዲስ አበባ ፖሊስ እንግልትና ድብደባ ተፈጸመብኝ አለች

የአሃዱ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ትእግስት ታንቱ ”በአዲስ አበባ ፖሊስ” እንግልትና ድብደባ ተፈጸመብኝ አለች

የአሃዱ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ትግስት ታንቱ ”ለምን ፎቶ አነሳሽ” በሚል በአዲስ አበባ ፖሊስ ድብደባ ደርሶባታል። ትግስት በፌስቡክ ገጿ ሁኔታውን እንዲህ ታስረዳለች።

”በምን ምክንያት ነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰድሺው ላላችሁኝ
ጥዋት 3:00 ገደማ ቢሮ ልገባ ታክሲ ይዠ ፒያሳ ደረስኩ ኦይል ሊቢያ አካባቢ ግርግር ተፈጥሮ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል። እኔም ሰዎች ወደተሰበስቡበት ተጠጋው ከዚያ ማህል ላይ አንድ ወጣት እድሜው በግምት 28 30 የሚሆነው የኢትዮጵያን ኮከብ የለለውን ባንዲራ ይዞ ይገኛል ይህን ወጣት ባንዲራ ለምን ያዝክ በሚል ከፖሊሶች ጋር ነው ግርግር የተፈጠረው ።

ፖሊሶቹም ልጁን ” ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንሂድና እዛው እናወራለን ” ሲሉት
አልሄድም ምንም አላደረኩም በሚል ነገሩ እየተካረረ መጣና መምታት ጀመሩ ቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች አትመቱትም በሚል ተከራከሩ ከዛም ከዚህም ፎቶ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ አይናቸው ያረፈው እኔ ላይ ሆነ እንጂ ሶስት ፖሊሶች መጥተው ” ፎቶ ማንሳት ወንጀል ነው አንቺም ትታሰርያለሽ!ወደ ፖሊስ ጣቢያ ትሄጅያለሽ!”ብለው አዋከቡኝ።እየገፈተሩና እየጎተቱም ወደ መኪናቸው አስገቡኝ።ባንዲራ የያዘውን ወጣትና እኔን ይዘው ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ወዳለው ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱን ።ከዚያም በቁጥር 6 የሚሆኑ ፖሊሶች እየተቀባበሉ ክፉኛ ደበደቡት!ወደ እኔም ዞረው ሁለቴ በጥፊ ከመቱኝ በኋላ ” ሴት መሆንሽ ነው ያተረፈሽ! ” ብለውኝ ተበታተኑ።

መርማሪ ፖሊስ ወደ ውስጥ እንድገባ አዞኝ ገባሁ፣ አንዱ መጥቶ ” ባልደራስ ነው የላከሽ! ” ሲላት ሌላኛው ደግሞ ” ልታስበጠብጪ ፈልገሽ ነው!” ብለው
ያነሳውትን ፎቶ አጠፉ። የማስጠንቀቂያ አይነት ሰተውኝ ተለቀቅኩ።”