በድንገት የተቋረጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነገ ረፋድ መግለጫ ይሰጣል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በ6 የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ተመድበው ይሰማራሉ

  የምልአተ ጉባኤው መግለጫ እና ለባለሥልጣናቱ የሚላኩት ደብዳቤዎች ቢዘጋጁም፣ በትክክለኛ መረጃዎች ተደግፈው እስኪጠናከሩ ድረስ ለነገ ማደሩ አስፈልጓል፤ የምልአተ ጉባኤው አባላት፣ ከትላንት ጀምሮ በ6ቱ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት የተገደሉና የተጎዱ ምእመናንን፣ በጥቃት ከበባ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያንን ሪፖርቶች እና መረጃዎች እያሰባሰቡ ነው፤ የባሌ፣ የአርሲ፣ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የምሥራቅ ሸዋ፣ የሻሸመኔ እና የድሬዳዋ አህጉረ ስብከት ሓላፊዎች፣ ዝርዝር የጉዳት …