በኦሮሚያ ክልል ስራ አጥ ወጣቶች ለእኩይ አላማ አራማጆች መጠቀሚያ ሆነዋል ተባለ።

ሥራ አጥነት የጸጥታ ችግሩን እንዳባባሰው ተገለፀ
(ኢ.ፕ.ድ)

በምዕራብ ኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ባለመስፋፋቱ በብዛት ወጣቱ ተምሮ ሥራ አጥ መሆኑንና ሂደቱም በእኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ዓላማ እንዲከተሉ ማድረጉን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስታወቀ።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በተለይ ከጋዜጣው ሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በቅርቡ የተወሰደውን መረጃ ዋቢ በማድረግ በምዕራብ ወለጋ ብቻ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸው ወጣቶች ቁጥር ከስድስት ሺህ በላይ ደርሷል።

በዚህ የተነሳ አንዳንድ ወጣቶች በእኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ዓላማ መከተላቸውን እና የጸጥታ ችግሩ እንዲባባስ ማድረጉን ያነሱት የዞኑ አስተዳዳሪ ችግሩን ለመቅረፍ ከሰላም ማስከበር ጎን ለጎን የስራ እድሎች የሚሰፉበት አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=21155