ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ከዓለም አቀፍ ውድድሮች ታገደ

በአፍሪቃ ጨዋታዎች የ10 ሺህ ሜትር ሻንፒዮን ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ብርሃኑ ፀጉ መታገዱን ተዘገበ ። አሾሲትድ ፕሬስ አትሌት ብርሃኑ የታገደዉ ጉልበት ሰጭ መድኃኒት ጋር በተያያዘ መሆኑን የአትሌቲክስ ማሕበርን ጠቅሶ ዘግቦአል።

አትሌቱ በተደረገለት ምርመራ EPO የተሰኘዉ ንጥረ ነገር በደሙ መገኘቱ እና ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑ ተነግሮታል። አትሌት ብርሃኑ ባለፈዉ ነሐሴ በሞሮኮ የተካሄደዉ የአፍሪቃ ጨዋታዎች ሻንፕዮን ሲሆን 19 ዓመቱ ነበር። ባለፈዉ ዓመት በኮፐን ሃገን የተካሄደዉን ግማሽ ማራቶን በሦስተኝነት ነበር ያጠናቀቀዉ።

ያኔ በኮፐንሃገኑ የትሌቲክስ ዉድድር ኬንያዊዉ አትሌት ጊዮፍሪ ካሙረር የዓለም ሪኮርድን አስመዝግቦ ነበር። በአሁኑ ጊዜ የአትሌቲክስ ማሕበር አትሌት ብርሃኑ ፀጉን በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ከዓለም አምስተኛ በ 10 ሺህ ደግሞ 19ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል።  – አሾሲትድ ፕሬስ