DW : በምእራብ ኦሮሚያ በመንግስት እና ኦነግ ሸኔ በሚባሉት ኃይሎች መካከል በሚደረገው ውጊያ ህዝቡ ተጎጂ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጡ። የኦሮሚያ ፖሊስ በአካባቢው ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ አካባቢው እንዳይረጋጋ የሚያደርገው ኦነግ ሸኔ ነው ሲል ይከሳል።አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው በኦነግ ሸኔ ስም ፖሊስ ይወስዳል ያሉት እርምጃ ሰላማዊ ሰዎችን ሰለባ እያደረገ ነው ይላሉ።DW ፖሊስ እና የአካባቢው ነዋሪዎችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል።