የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ዘርን መሰረት ያደረገ ነው የሚለውን የዜጎች መፈናቀልን እንዲያስቆም ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠንካራ ማሳሰቢያ አቀረበ። ፓርቲው ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫው፣ መንግሥት ለዜጎች መፈናቀል ተጠያቂ የሚባሉትንም ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቆ፣ ይህን ካላደረገ ግን አገር አቀፍ የህዝብ ንቅናቄ እንደሚጠራ ግልጽ አድርጓል።