እምቦጭን የማስወገዱ ጥረት

ከ5,300 ሄክታር የሚበልጥ የጣናን ሀይቅ ከፊል ሸፍኖ ከነበረው የእምቦጭ አረም መካከል 87% መወገዱን ያካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ። እንደ ባለስልጣናቱ ገለጻ፣ አረሙን በማስወገዱ ስራ ላይ ከ214,000 የሚበልጡ ሰዎች በነፃ አገልግሎት በመስጠት ተሳትፈዋል፤ በወቅቱ አረሙን በማሽን ለማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴ ጥሩ ውጤት አስገኝቷል።