አትድከሙ ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም – ለንደን/እንግሊዝ
ዘመድኩን በቀለ
በእንግሊዝ ከማንችስተር፣ ከሊድስ፣ ከኒውካስትል፣ ሀርድርስ ፊልድና ካርዲፍ የተዋሕዶ ልጆች ወደ ለንደን እየገቡ ነው። የለንደን ዝናብ እኚኚኚኚ ቢልም እነሱ እቴ ሰልፉ ሳይጀመር ዝማሬያቸውን እያፈሰሱት ነው።
ልጆቿ በለንደን መሰባሰብ ጀምረዋል።
• በታላቋ፣ በጥንታዊቷና በብሔራዊቷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ሁለንተናዊ መንግሥታዊ በደል ለመላው ዓለም ህዝብ የማሳወቅ ዘመቻ አካል የሆነ የተዋሕዶ ልጆች ሰልፍ አሁን ሊጀመር ነው።
• ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ወደ ለንደን እየተመሙ ነው።
• ድንኳን እየተጣለ ነው።
• አሁን በዚህ ሰዓት ለንደን ዝናባማ ብትሆንም የተዋሕዶ ልጆች እንኳን ዝናብ እሳት ለምን አይዘንብም በማለት ለእናት ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ተዘጋጅተዋል።
★ የአውሮጳ ዝናብ የሙከጡሪ ዓይነት ዝናብ አይምሰልህ፣ ጥርስ አለው። አኝ ነው የሚያደርግህ። አያ ጅቦ ነው። የእጅ እግር ጣት የሚያቃጥል እንደ እሳት ያለ ጠባይ ያለው ነው። ይሄን ተቋቁሞ ደጅ መዋል በራሱ ሰማዕትነት ነው።
መዝሙር 137 ከ ቁ 1-7 በለንደን ጎዳኖዎች ይጸለያል።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
² በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።
³ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።
⁴ የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
⁵ ተዋሕዶ ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።
⁶ ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
⁷ አቤቱ፥ በኢትዮጵያ ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።
⁸ አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።
⁹ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
Source — ዘመድኩን በቀለ