የኦርቶዶክስ አማኞች በደቡብ ክልል ለተቃጠሉና ጥቃት ለደረሰባቸው ቤተ ዕምነት ካሳ እንዲከፈላቸው የክልሉን መንግሥት ጠየቁ

VOA : የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ዙሪያ ከቤተክርስቲያንቷ ጋር በሃዋሳ ከተማ መከሩ።ቤተክርስቲያኒቷ በክልሉ በተቃጠሉና ጥቃት በደረሰባቸው ቤተ ዕምነት ካሳ እንዲከፈላቸው የክልሉን መንግሥት ጠይቀዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የተቃጠሉ በእምነት፣ ጥቃት የደረሰባቸው ካህናትና ምዕመን መጠንና የጉዳቱ መጠን በጥናት እንዲቀርብና መንግሥትም ጥናቱን ተከትሎ ምላሽ እንደሚስጥ ተናግረዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።