አምስት ክለቦች የፖለቲካ ስያሜ አላቸው በሚል የስያሜ ለውጥ እንዲያደርጉ ተነገራቸው

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፖለቲካ ገፅታ (ይዘት ) ስያሜ አላቸው በሚል የስያሜ (መጠሪያ) ለውጥ እንዲያደርጉ ከለያቸው አምስት ክለቦች መካከል ፋሲል ከነማ  ተካቷል ።

ፌዴሬሽኑ ፋሲል ከነማ የሚለው ጎንደር ከተማ በሚል ስያሜ እንዲጠራ ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን በተመሳሳይ
ጅማ አባጅፋር ወደ ጅማ ከተማ
መቀለ 70 እንደርታ ወደ መቀለ ከተማ
ስሁል ሽሬ ወደ ሽሬ ከተማ
ወልዋሎ ወደ አድግራት ዩንቨሪስቲ
ወደ ሚል ስያሜ እንዲለወጡ በቀጣዩ የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡

በርካቶች ፋሲል ከነማ የሚለው ስያሜ ጎንደር ከተማ በሚል ስያሜ ቢተካ ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ ቢኖራቸውም ሌሎች በበኩላቸው የክለቡ ስያሜ መለወጥ የለበትም በሚል እየተከራከሩ ነው ።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አመራሮች የክለባችን ስያሜ የቆየና ፖለቲካዊ ይዘትም ሆነ ገፅታን አልተላበሰም ።

በተጨማሪም የክለቡ ስያሜ (መጠሪያ) ” የከተማ ነዋሪዎች ማህበር” የሚል መጠሪያ ያለው በመሆኑ እንድንቀይር አንገደድም የክለባችን ስም ከላይ ከተጠቀሱት ክለቦች ዝርዝር መካተቱም አግባብነት የለውም ብለዋል ።

በቀጣይስ የክለቡ አመራሮች በአቋማቸው ፀንተው ተወዳጁ “ፋሲል ከነማ” የስያሜ ለውጥ ሳያደርግ ይቀጥላል ?

ወይስ የስም ለውጥ ተደርጎ በአዲስ መጠሪያ “ጎንደር ከተማ” ይሆናል የሚለው በቀጣይ ይጠበቃል ።

via – ፋሲል ከነማ