እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን እስከ ነገ ጠዋት 3:00 ይቅርታ እንዲጠይቁ ቅ/ሲኖዶስ ገደብ ሰጠ፤ ጥያቄአቸው በመሪ ዕቅዱ ትግበራ ማሕቀፍ እንደሚፈታ ገለጸ

ጋዜጣዊ መግለጫው ለረፋድ 4፡00 ተቀጥሯል የጥያቄአቸው መነሻ በኾኑት በኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት፥ የስብከተ ወንጌል፣ የዕቅበተ እምነት እና የአገልጋዮች እጥረት… ወዘተ. ችግሮች ላይ ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መግባባት ላይ ቢደረስም፣ ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሰጠበት ጉዳይ እንደኾነ እያወቁ፣ “የክልል ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናደራጃለን፤” ማለታቸውና የቋሚ ሲኖዶሱን ክልከላ ተላልፈው የሚዲያ መግለጫ መስጠታቸው ስሕተት እንደኾነ በብፁዓን አባቶች ተገልጾላቸዋል፤ …