" /> በደቡብ አፍሪቃ የድረሱልን ጥሪ ያሰሙት በገፍ የታሰሩ ኢትዮጵያዉያን እየተፈቱ ነዉ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በደቡብ አፍሪቃ የድረሱልን ጥሪ ያሰሙት በገፍ የታሰሩ ኢትዮጵያዉያን እየተፈቱ ነዉ

DW : በደቡብ አፍሪቃ የድረሱልን ጥሪ ያሰሙት በገፍ የታሰሩ ኢትዮጵያዉያን እየተፈቱ ነዉ ሲሉ ለዶይቼ ቬለ«DW» ገለፁ። በጆሃንስበርግ ከተማ ነጋዴና የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተወካይ አቶ ታደሰ የማነ እንደተናገሩት በፕሪቶርያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቦታዉ ላይ በመገኘት እና የሕግ ሰዎችን በማቆም፤ ሕጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸዉና እስር ላይ የነበሩ ከመቶ በላይ ኢትዮጵያዉያን መለቀቃቸዉን ተናግረዋል።

አቶ ታደሰ እንደሚሉት የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሕገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ወደ 600 የዉጭ ሃገር ዜጎች ታስረዋል ሲሉ ቢዘግቡም የታሰሩት እስከ 1000 ይገመታሉ ብለዋል። በሌላ በኩል ሕገወጥ ከተባሉ የዉጭ ሃገር ዜጎች ላይ የተወረሱ እቃዎችን ሊሸጡ ሲሉ ተገኙ የተባሉ ሰባት የፖሊስ መኮንኖች መታሰራቸዉን የተለያዩ ድረ ገጾች አስንበብበዋል።

Image result for south africa police arrests ethiopians


የመረጃ ቲቪ አባል ይሁኑ - JOIN US