በኢትዮጵያ የሚታየው ቀውስ ተስፋ ሰጪ መፍትሄ እንዲያገኝ የብሔር ጡዘት መወገድ እንዳለበት እና የሕገ መንግሥቱ መሻሻልም ወሳኝነት እንዳለው ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የሚታየው ቀውስ ተስፋ ሰጪ መፍትሄ እንዲያገኝ የብሔር ጡዘት መወገድ እንዳለበት እና የሕገ መንግሥቱ መሻሻልም ወሳኝነት እንዳለው ተገለጸ። በሀገሪቱ በማንነት ፖለቲካ ላይ ብቻ ትኩረት መደረጉ ከሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲራቅ አድርጓልም ተብሏል።በዛሬው ዕለት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራት እና በሀገር ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ አካላት በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ፣ ዶክተር ኮንቴ ሙሳ፣ ዶክተር መላኩ ተገኘ እና አቶ ሙሼ ሰሙ የመነሻ ንግግር አድርገው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል። ውይይቱን ያዘጋጀው ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ነው


► መረጃ ፎረም - JOIN US