በአምቦ ከ5መቶ በላይ ሰዎች ታሰሩ ፥ ፖሊስ አላውቅም ብሏል።

VOA : በአምቦ ከ5መቶ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፖለቲካ ኃላፊም አባላትና ፣ ደጋፊዎቼ እንዲሁም አመራሮቼ ታስረዋል ብሏል፡፡ የከተማው ፖሊስ መምሪያ የታሰረ ሰው የለም ሲል አስተባብሏል፡፡ የክልሉ ፀጥታ ቢሮና ፖሊስ ኮሚሽን መልስ እንዲሰጠን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡