የታሰሩ ግለሰቦች በምግብ እጥረትና አያያዝ ጉድለት እየታመሙ መሆናቸውን ገልፁ፡፡

በሰንቀሌ ፖሊስ ማሰልጠኛ የሚገኙ አንዳንድ የታሰሩ ግለሰቦች በምግብ እጥረትና አያያዝ ጉድለት እየታመሙ መሆናቸውን ገልፁ፡፡መንግሥት በቶሎ ይልቀቀን እስኪለቀንም አያያዛችንን ያሻሽልልን ሲሉ አመልክተዋል፡፡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አባላቶቹ መታሰራቸውንና ስለ ሰብዓዊ አያያዛቸው ለማወቅ መቸገሩን አስታውቋል፡፡የኦሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የእስረኞቹ ሰብዓዊ አያያዝ ላይ ስለሚነሳው ቅሬታ አስተባብለዋል፡፡