ኦሮሚያ ውስጥ ቻይናውያን ላይ ተሰነዘረ በተባለ ጥቃት አንድ ቻይናዊ ተገደለ

ባለፈው እሁድ ኦሮሚያ ውስጥ ቻይናውያን ላይ ጥቃት ተሰነዘረ ስለተባለው ጉዳይ: ( ኤሊያስ መሰረት )

የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው እሁድ ቻይናውያን ላይ ደረሰ ስለተባለው አደጋ ይህን ብለውኛል:

“ድርጊቱ የተፈፀመው አዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ አቅራቢያ እሁድ አንድ ሰአት ገደማ ነው። እራት ከበሉ በሁዋላ በግሩፕ ወጡ። የሄዱበት ቦታ ከፓርኩ ሶስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያለ ሲሆን ጭለማ እና ገደላማ ስፍራ ነው። የአካባቢው ሰው እንኳን አይሄድበትም። ለምን ወደዛ እንደሄዱ ገና እየተጣራ ነው። ከዛም ቻይናዎቹ እርስ በርስ እንደተወጋጉ ሟቹ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ተናግሮ ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን ሌሎች ሰዎች እንዳረጉት ለማስመሰል ተሞክሯል። በጥርጣሬ የተወሰኑ ቻይናውያንም፣ የአካባቢ ሰዎችም ተይዘዋል። ዝርፊያ ስለተባለው ግን አላውቅም እነሱም ተዘረፍን ብለው ሪፖርት አላደረጉም።”

China News እንደዘገበው ኦሮሚያ ውስጥ (ቦታ አልተጠቀሰም) ባለፈው እሁድ ስድስት ጥቃት አድራሾች በኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ባደረጉት እንቅስቃሴ ቢያንስ አንድ ቻናዊ እንደተገደለ፣ ሌላው እንደቆሰለ እና ሰባት ሌሎች እንደተዘረፉ የቻይና ኤምባሲን ዋቢ አድርጎ ፅፏል።