የትግራይ መስተዳደር የኤፈርት ንግድ ኩባንያዎች አክሲዮንን ለመሸጥ ማቀዱ ድጋፍና ተቃዉሞ ገጥሞታል።

ዉጪ ሐገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የንግድ አክሲዮን እንዲገዙ ኤፈርት ጠየቀ

DW : የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (በትግርኛ ምህፃሩ ትእምት) የሚያስተዳድራቸዉ ሶስት ኩባንዮች አክሲዮንን ለሽያጭ እንደሚያቀርብ የክልሉ መስተዳድር አስታወቀ።የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀዉ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽንና ትራንስ ኢትዮጵያ የተባሉትን ኩባንዮች ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ አቅዷል።የሶስቱን ኩባንዮች አክሲዮንን ዉጪ ሐገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዲገዙ ተጠይቀዋል።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ እንደሚለዉ በትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ትእምት) ኩባንዮች ላይ የክልሉ መስተዳድር የሚያደርገዉ ለዉጥ ድጋፍና ተቃዉሞ ገጥሞታል።