የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ን በገንዘብ ረድታችኋል በሚል ተጠርጥረው ተይዘው የነበሩ በዋስትና ተለቀቁ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን በገንዘብ ትረዳላችሁ በሚል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ 56ቱም ተጠርጣሪዎች ከ10 ቀን ቆይታ በኋላ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ተለቀዋል፡፡

በሜታ ወረዳ ሥር በሚገኙት የቁሉቢና ጨለንቆ ከተሞች ባልታወቀ ሰዓትና ቦታ ተሰብስባችሁ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ን በገንዘብ ረድታችኋል በሚል ተጠርጥረው ተይዘው የነበሩ 8 የቁልቢ እና 48 የጨለንቆ ከተማ ነዋሪዎች ዋስትና ተፈቅዶላቸው ከእስር ተፈተዋል፡፡

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE