አዲስ አበባ ላይ የሚፈርሱ ቤቶች ሕገወጦች ናቸው ቢባልም ሐቁ ሌላ ነው ሲሉ ነዋሪዎች እየከሰሱ ነው።

አዲስ አበባ ላይ የሚፈርሱ ቤቶች ሕገወጦች ናቸው ቢባልም ሐቁ ሌላ ነው ሲሉ ነዋሪዎች እየከሰሱ ነው።(ምንሊክ ሳልሳዊ)
 
በልማት ስም የሚደረጉ መንግስታዊ ወንጀሎችን እያንዳንዱ ዜጋ የመቃወም ግዴታ አለበት ። የትላንትና የሕወሓት ወንጀሎች በለውጥ ሽፋን ዛሬ ላይ በኦሕዴድ ሲደገሙ ዝምታ መምረጥ አሊያም አደርባይ መሆን ያሳፍራል።የሕዝብ ውክልና የሌለው አስተዳደር በነዋሪዎች ላይ እየወሰደ ያለው ሕገወጥ ርምጃ ሕጋዊ ዜጎችን ሕገወጥ በማለት ሜዳ ላይ በማፍሰስ ለዜጎች ደሕንነትና መብት ደንታ ቢስ መሆኑን በጉልበቱ በመጠቀም እያሳየን ይገኛል።
 
በሕዝብ ሕጋዊ ውክልና የሌለው የታከለ ኡማ አስተዳደር በወንዞች ዳርቻ ልማት 30 ሺሕ ነዋሪዎችን ለማስነሳት እንቅስቃሴ እንደጀመረ እየተናገረ ነው። ሕገወጡ የታከለ ኡማ አስተዳደር ሕገወጦችን የማፍረስ ስራ እሰራለሁ ሲል ከሞራል አንፃር እጅግ አስነዋሪ ነው ።
 
ሕጋዊ ነዋሪዎችን ሲያስነሱ ከዚህ ቀደም ሕወሓት የሰራውንና ለፖለቲካ ፍጆታ የተጠቀመበትን የነዋሪዎች ብተና ዖዴፓ ዖሕዴድም ሊደግመው መሆኑ የሕብረተሰቡን የማሕበራዊ እሴት በማደፍረስ ከእድርና አብሮ ከኖረው ሕዝብ ነጣጥሎ የማፈናቀል ስራ ሊሰራ መሆኑ ውጥረቱን አብሶታል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የሚፈርሱት ቤቶች በ15 ቀናት ውስጥ በከተማዋ በህገወጥ መንገድ የተገነቡትን ነው ቢልም ነዋሪዎቹ ግን ሃቁ ሌላ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። መረጃዎቹ እንደሚጠቁሙት ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በየወረዳዎቹ አመራሮች የተሰጠን መመሪያ ከ7 አመትና ከዛ በላይ የኖርንበት ቤታችንን በ15 ቀናት ውስጥ ራሳችን አፍርሰን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ነው።አመራሮቹ ይሄን ሲሉም ህግ ህግ ነውና መከበር አለበት ስለዚህ ይሄንን ተግባራዊ እናደርጋለን ሲሉ ነው ለነዋሪዎቹ መመሪያ ያስተላለፉት።
 
መረጃዎቹ ክረምት ሲመጣ ተጠብቆ የሚካሄደው ቤት ማፍረስና ማፈናቀል በደሃው ህዝብ ላይ እንዲፈጸም የሚደረግበት አግባብ አይገባንም ይላሉ ነዋሪዎቹ።በተለይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ የተነገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት በአካባቢው በ15 ቀናትም ሆነ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የተካሄደ ህገወጥ ግንባታም ሆነ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ የለም።ይሄ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ቤታችሁን አፍርሱ የሚል መመሪያ መተላለፉ ህጋዊ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ ነዋሪዎቹ።ይሄን መመሪያ በደሃው ህዝብ ላይ የሚያስተላልፉ አመራሮች በሌብነት የተገነቡ ቤቶችን ለማስፈረስ ግን ስልጣናቸውን ሲጠቀሙ አይታዩም ሲሉ ይከሳሉ።መረጃዎቹ እንደሚጠቁሙት
 
የሕዝብ ውክልና የሌለው አስተዳደር በነዋሪዎች ላይ እየወሰደ ያለው ሕገወጥ ርምጃ ሕጋዊ ዜጎችን ሕገወጥ በማለት ሜዳ ላይ በማፍሰስ ለዜጎች ደሕንነትና መብት ደንታ ቢስ መሆኑን በጉልበቱ በመጠቀም እያሳየን ይገኛል። ይህ አይነት አደገኛ አካሔድ ዛሬ ላይ የሚያዋጣ መስሎ የሚታየው መስተዳደር ነገ ላይ ዋጋ ይከፍልበታል።(ምንሊክ ሳልሳዊ) #MinilikSalsawi

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE