ኦርቶዶክስን በኑፋቄ ዘውጎች የከፋፈለው የሕዝብ ቆጠራ ቅጽ እንዲታረም ቅ/ሲኖዶስ በጥብቅ አሳሰበ፤“ፍጹም የቤተ ክርስቲያን ስም ብቻ ነው!”

የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽኑ፥በኦርቶዶክስ ስም አንጻር፣ በጉባኤ ተወግዘው የተለዩትን “ቅብዐት እና ጸጋ” በማጫፈር፣ ‘ኦርቶዶክስ ቅብዐት’ እና ‘ኦርቶዶክስ ጸጋ’ የሚል የምዝገባ ቅጽ አካቷል፤ “ቅብዐት” እና “ጸጋ” ለተባሉ መናፍቃን፣ በዘዴ ዕውቅና በመስጠት አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን የሚከፋፍል ነው፤በሕግም የሚያስጠይቅ በመኾኑ ቅጹ በአስቸኳይ እንዲታረም በጥብቅ አሳሰበ! “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ”፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ተቋም የሚጠራበት ፍጹምና አጠቃላይ መጠሪያ ስም …