ለዋና ኦዲተር መስርያ ቤት ምላሽ ያልሰጡ 53 ተቋማት በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ስር የሚገኙና በኦዲት ግኝት ጉድለት የተገኘባቸው እና ለከተማዋ ዋና ኦዲተር መስርያ ቤት ምላሽ ያልሰጡ 53 ተቋማት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላለፈ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ እነዚህ ተቋማት በከተማው ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና ምክር ቤት በፀደቀው ዓዋጅ መሠረት በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ በኦዲት ግኝቱ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠየቁም በወቅቱ ምላሽ ለመስጠት ስላልቻሉ ተቋማቱ በህግ እንዲጠየቁ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

እነዚህ ከ2008-2010 ዓ.ም ምላሽ ያልሰጡ 53 ተቋማት በዋና ኦዲተር መ/ቤት ና በከተማው ም/ቤት በሚደነግገው መሠረት ምላሽ እንዲሰጡ የሁለት ወር የጊዜ ገደብ ቢሰጣቸውም ምላሽ እንዳልሰጡ ታውቋል፡፡

ምንጭ:- የከንቲባ ፅ/ቤት

Image may contain: one or more people