ለቤተ ክርስቲያን እመርታ የተመዘገበበት የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ3 ዓመታት ሪፖርት ለቅ/ሲኖዶስ ቀረበ፤ “በፈተናና ተግዳሮት መካከል የተሠሩ ናቸው!”

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ገቢ፣ ከ3 እጥፍ በላይ ተመንድጓል፤ በቀጣይነት የሚያሳድጉት ልማታዊ ተግባራት ተከናውነዋል፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ሕጉን ጠብቀው የተፈጸሙ ናቸው፤ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ያረጋገጡ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፤ ጨረታን ባሸነፉ የውጭ ኦዲተሮች በየዓመቱ ተመርምሯል፤ *** የሠራተኛው አቅም፣ በተከታታይ ሥልጠናዎች ተገንብቷል፤ በደመወዝ ጭማሪ እና የእርከን ማስተካከያ ተጠቃሚ ኾኗል፤ የ2 ዙር የሰላምና የስብከተ ወንጌል ስምሪትም አትራፊ ነበር፤ ያገዟቸውን አባቶች አመሰገኑ፤ …