“ገበታ ለሸገር” – የዝግጅቱ ድባብ – የሁነቱ ፋይዳ – በታዳሚ ዐይን

VOA

“ገበታ ለሸገር” በሚል የተሰየመ ፣ገቢው አዲስ አበባን ለማስዋብ የሚውል  የእራት ዝግጅት በአጤ ምኒሊክ  እልፍኝ ውስጥ ተከናውኗል፡የእራቱ ታዳሚዎች በታሪካዊው ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም እያንዳንዳቸው 5ሚሊየን ብር ከፍለዋል፡፡በዚህ ዝግጅት ላይ ታዳሚ ከነበሩት እና ፣ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አዲስ ግብር የተበላበትን ታሪካዊ እልፍኝ ለታዳሚኑ ሲያስጎበኙ ያመሹት የኪነ-ህንጻ ባለሙያው ዮሃንስ መኮነን የዝግጅቱን ድባብ እንዲሁም በእሳቸው ምልከታ የሁነቱ ፋይዳ ነው ያሉትን አካፍለውናል፡፡