የዝዋይ ሀይቅ በእምቦጭ አረም እየተጠቃና ለጥፋት እየተጋለጠ መምጣቱ ተሰማ

ሐይቁ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በእምቦጭ አረም እየተጠቃና ለጥፋት እየተጋለጠ መምጣቱን በኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የባቱ ዓሳና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል መረጃ ይጠቁማል ።

በኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የባቱ ዓሳና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማእከል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ለማ አበራ ለኢዜአ እንደገለፁት ከዝዋይ ሀይቅ ከአራት ዓመታት በፊት በዓመት በአማካይ ከ4ሺህ 500 እስከ 6ሺህ ቶን ዓሳ ይመረት ነበር ።የዝዋይ ሀይቅ ጥልቀቱ በ3 እጥፍ ምርታማነቱ ደግሞ በ4 እጥፍ ቀንሷል“አሁን ግን የሐይቁ የዓሳ ምርት ከ1ሺህ ቶን ያነሰ ነው”ብለዋል ።

የሐይቁ ውሃ ጥልቀቱም ቢሆን ከ12 ሜትር ወደ 4 ሜትርና ከዚያ በታች መውረዱን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።“ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በሐይቁ የእምቦጭ አረም እየተስፋፋ ነው” ያሉት የምርምር ማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ይህም ሐይቁ እየተበከለ መምጣቱን የሚያሳይ እንደሆነ አስረድተዋል ።

የዝዋይ ሐይቅ ብቻ ሳይሆን በስምጥ ሸሎቆ የሚገኙ ሌሎች ሃይቆችና የውሃ አማራጮች እየተጎሳቆሉና እየደረቁ መሆናቸውን ጠቅሰው አካባቢው ለእሳተ ጎሞራ እንዳይጋለጥ ሃይቆቹን መጠበቅ የውዴታ ግዴታ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል ።

ENA/ኢዜአ