ፌስ ቡክ በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፉ ቪዲዮች በሚቀሰቀስ ቁጣ የሚደርሰውን ውድመትና እልቂት ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Facebook imposes restrictions on live-streaming to prevent future abuse

‘Our goal is to minimize risk of abuse on Live,’ Guy Rosen said

ፌስ ቡክ በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፉ ቪዲዮች በሚቀሰቀስ ቁጣ የሚደርሰውን ውድመትና እልቂት ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ህግን ተላልፈው የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የቀጥታ ስርጭት እንዳያስተላልፉ ሊያግድ መሆኑን የካምፓኒው ምክትል ፕሬዚዳንት ጉዋይ ሮሰን ገልጸዋል፡፡

“በቅርቡ በኒውዝላንድ የሽብር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ማህበራዊ ትስስሩ የሚላለፉ መረጃዎች አይነትና ይዘት ላይ ገደብ መጣል እንዳለብን ተረድታናል” ነውም ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ፡፡

የቀጥታ ስርጭት እገዳው አንድ ቦታ ላይ ግጭት ሲከሰት ለበቀል እርምጃ ቅስቀሳ በማድረግ ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡

ከአሸባሪ ቡድኖች የሚለቀቁ መግለጫዎችን ማጋራትም የእገዳው አካል እንደሚሆን ያመላከቱት ጉዋይ ሮሰን በመጭዎቹ ሳምንታት ተግባራዊ እንደሚሆንም ነው የጠቆሙት፡፡

ምንጭ፡-  ኤአፍፒ

https://edition.cnn.com/2019/05/14/tech/facebook-livestream-changes/index.html

https://www.theverge.com/2019/5/14/18623892/facebook-restrictions-live-streaming-prevent-future-abuse-christchurch-new-zealand


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE