ሕገ ወጥ የተባሉ ሰነድ አልባ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ ተደረገ ።

ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ማሟላት ያልቻሉ እና በፍጹም ምንም ማቅረብ ያልቻሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ ተደረገ ።


ኤጀንሲው በቁጥር 01/77/1582/11 በቀን 19/06/2011 ዓ.ም በፃፈው ደበዳቤ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ህጋዊ ሰነዶችንና መስረጃዎችን እንዲያሟሉ ማሳሰቡ ይታወቃል፡፡
በዚሁም መሰረት ፦
1) በተጠየቁት መሰረት ሙሉ ለሙሉ ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ያቀረቡ፣
2) ያቀረቡት ሰነድ በከፊል ያልተሟላ እና
3) ፈጽሞ ምንም ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ያላቀረቡ ይገኙበታል።
ይህን መነሻ በማድረግ ህጋዊ ሰነዱን በከፊል ያላሟሉም ሆነ እና ፈጽሞ ምንም ዓይነት ሰነድ ያላቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የያዙትን ተማሪዎች ብቻ ከማስጨረስ ውጪ ኤጀንሲው የጠየቀውን ህጋዊ ሰነድና መስረጃ ሙሉ ለሙሉ እስካላቀረቡ ድረስ አዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ የማይችሉ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ውሳኔውን ያስተላልፏል።
በመሆኑም ተማሪዎች፣ ወላጆችና መላው ህብረተሰብም ይህን አውቆ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኤጀንሲው በጥብቅ ያሳስባል።

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ
ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም