የባህር ዳሩ የብአዴን ኮንፈረንስ መበጣበጡን ቀጥሏል

ቲም ገዱ ሰይፍ በሆነ አንደበት ሕዝቤን ማለት ጀምሯል፤ ፍርሃት ተገፎ በድፍረት ተተክቷል፥ ብአዴን አደጋ ላይ ነው፥ ትልቁ ህዝብ አማራ ባህርዳር ላይ ዱካው እየተሰማ ነው።

ከጥሩነህ ይርጋ ገፅ የተወሰደ

በረከት ስምኦንና ጥንቅሹ ከዛ አምባዬ የሚባል ወፍጮ ፊት ጋር ነገር ከብዶባቸው ተደናግጠዋል ይላል ዘገባው።

የብአዴን ኮንፈረንስ የትናት ውሎ፦ (ረዘም ያለ ነው። ፅሁፉ ትንሽ ብቻ ነው የተስተካከለ እንጅ እንደወረደ ነው። )

የብአዴን ኮንፈረንስ በሰሞኑ ስብሰባ ከተናጋሪዎች ውስጥ ሁለት የኃይል አስላለፍ እንዳለ አመላከቷል፤

#የለውጥ ፈላጊ ቡድን

ዶ/ ር አንባቸው መኮነን
ፀጋ አራጌ
ላቀ አያሌው
ንጉሱ ጥላሁን
እዘዝ ዋሴ
(በትናንትናው መድረክ በረከትን ቀድሞ ያዋረደው ነው)

ጌታቸው ጀንበር እና ሌሎች ወጣቶች ሲሆኑ

#ከለውጥ ናፋቂው በተቃራኒ #ለማፈራረስ የተሰለፉት

በረከት ስምኦን
ታደሰ ጥንቅሹ
ከበደ ጫኔ
ዝማም አሰፋ
ህላዊ ዮሴፍ
አዲሱ ለገሰ
ጌታቸው አምባየ
እና ሌሎችም ሽማግሌዎችና ተላላኪዎች

የመድረኩ አጀማመር
በቀደም እለት ሽማግሌዎቹ ሲናገሩ ከቆዩ በኃላ ብዙም መልስና ክርክር ተደርጎ ነበር ማለት አይቻልም፤ እናማ እላችኃለሁ ተወዝፎ ያደረው ውይይት ቀጠለ፤ ከዚህ ቀጥሎ የትናንት ውሎ በተመለከተ ዋና ዋና የምላቸውንና ሰው ቢሰማቸው ይተቅማሉ ያልኳቸውን ሃሳቦች ብቻ እንዳለ እና እንደወረደ አቀርባላችኋለው ድራማውን ተከታተሉ፤

#ፀጋ አራጌ፡ –

ከሰሜን ወሎ ፤ ከነ አለምነው መኮንን መንደር የተገኘ ጀግና፤ አሁን በክልሉ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡ የመጀመሪያውን እድል ወሰደ፤ ሽማግሌዎቹን እንዳልሆኑ አደረጋቸው ፤ የሚበቃውን ተናገረ፤መቸም እውነት ነው የምላችሁ መጫዎቻ ነው ያደረጋቸው፤

ዶ/ር #አንባቸው መኮንን

( የቴወድሮስ ወራሽ፤የገብርየ ኩልኩል)፤ ሁለተኛውን እድል ወሰደ፤ እንዲህም አለላችሁ፤ በእኛ የስልጣን ዘመን የአማራ ወጣት አልቋል፣ በአማራ ህዝብ በደረሰው ግፍ ሁሉ ይቆጨናል፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፍኖናል፤ከብዶናል፤ ታስረው የነበሩ የአማራ እስረኞችን ለማስፈታት ቡዙ ተሰቃይተናል ፤ ከዚህ በኃላ አፍረናል ወደ ኃላ አንመለስም፡፡ ለነገሩ እኮ እናንተ ሰዎች ( እነበረከትን መሆኑ ነው) ሽፈራው ሽጉጤን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጋችሁ አስመርጣችሁ ልታስጁን ነበር፤

#ንጉሱ ጥላሁን

( የምኒሊክ ግርፍ፤ የሽዋዎች ዘር)፤ የአማራ ብሄርተኝነት እንዲህ ገኖ የወጣው መነሻው በደል ስለሆነ ነው፤ አማራ ተገፍቶ ነው ወደዚህ የደረሰው፤የሀብት ክፍፍሉ ላይ የፍትሀዊነት ችግር አለ ለሚለው ክስ፤ ክሱ በግብረ ሀይል ይጣራ የሚባለው ፤ ፌዝ ነው፤ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ጉዳዩንም የህውሀቱ ደብረ /ጺወን በአደባባየረ ያመነው ጉዳይ ሁኖ እያለ ግብረ ሀይል ተቋቋመ አልተቋቋመ ምን ለውጥ ሊመጣ ነው፡፡ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ላይ የነበረው ሽኩቻም ችግር ነበረበት፤ ኃይለማሪያምና ሽፈራው ሽጉጤ አባዱላን ጠርተው ከምርጫ ውጭ ጠቅላይ ሚስትር እንዲሆን አወያይተውት ነበር፤ ከዚህ ጀርባም የጀኔራሎች እጅ ነበረበት፤ ማስፈራራትም ይሰሩ ነበር ፡፡ እኔ በኃይማኖቱ በኩል ቡዙም አክራሪ አማኝ ባልሆንም፤ ዶ/ር አብይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው፤ በእግዚያብሄር ነው፤ በእግዚያብሄር ታዞ የመጣ ነው፤ በትግሉ ነው እዚህ የደረሰው፤ የተቃወሙትም በዋነኛነት ህውሀቶች ናቸው፡፡

በረከት አሁን ያለው የብአዴን አመራር ስልጣንን ለግል ጥቅሙ እያዋለ ነው ብለሀል ፤ ግን እኮ እናንተ ( በረከትን ከነቡድኑ መሆኑ ነው ) ገዱ ከስልጣን ይውረድ ነው የምትሉን ፤ እሄን ደግሞ አንቀበላችሁም አልናችሁ፤ በቃ ተሸነፋችሁ፡፡ ግን- ግን እናንተ ሰዎች ሁሌ መተካካት ላይ ነው እንዴ የምትጨቃጨቁት ( እሄም እነ ገዱን ለመግፋት ነው)፤ እስኪ መቸ ነው ስለ አማራ ህዝብ የትምህርት ፤የጤና፤የውሀና መሰረተ ልማት የተወያየነው? የልማት አጀንዳችንን እኮ አስራችሁብናል፡፡

#ላቀ አያሌው፦

ሰውየው ከወደ በላይ ዘለቀ ነው፤ አሁን የክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ቢሮ ኃላፊ ነው፤ እንደጉድ እሄን ሽማግሌ( በተለይም በረከትን) ሁሉ ጥባጥቤ ተጫወተበት እላችኃለሁ፡፡ ለነገሩ የበላይ ዘር ሁኖ ቢፈራ ነበር እንጅ የሚገርመው መድፈሩስ የአባቶቹ ነው፡፡ ላቀ በረከትን እንዲህ አለው፤ በረከት፤ አንዴ ከማእከላዊ ኮሚቴ ወጥቻለሁ ብለህ ትሄዳለህ፣ መካከሉ ላይ ደግሞ ተመልሰህ ትገባለህ፣ ያንተ ነገር እኮ ጨነቀን፡፡ ለካ አባዱላን ጠቅላይ ሚኒስትር ልታደርጉ ነው ለቅቂያለሁ ካልክ በኃላ ዙረህ ተመልሻለሁ ያልከን፡፡ወጥቻለሁ ካልክ በኃላ ለምንድን ነው የተመለስከው? አሁን ለምን እንደተመለስክ አውቄዋለሁ፣ ግን የተመለስክበትን ምክንያቱን አንተው እራስህ ተናገር፤ እኔ ባውቀውም ቀድሜ አልናገርም፡፡ እንዴው ለመሆኑ ለመሆኑ አቋምክን በኮንፈረንስ መድረክ ብቻ የምታቀርብ ለምንድን ነው ? በፍትሀዊት ተጠቃሚነት ላይ ያልታገላችሁበት ምክንያት ምን ነበር ?( እዚህ ላይ በረከት ላቀን አቋርጦ ጣልቃ በመግባት እኔ ያልታገልኩበት ወቅትና ቦታ የለም አለ)፤ ላቀ አጸፋውን መለስ፤ እሄነን ጉዳይ ከታገልክ እንግዲያው ከማርዠነብ ( ጠገዴ) ወደ ወልቃይትና ዳንሻ በመንገድ ስራ ላይ ተሰማርቶ ሲሰራ የነበረን ሁለት እስከባተር እስከዛሬ ድረስ ስራውን እንዲያቆም ሲደረግ ለምን አልታገልክም ? ሳቅ…… በሳቅ…….፡፡ ላቀ ይቀጥላል፤ የትግራይ ህዝብ ተነካ ብላችሁ እሂንን ያክል የምትጮሁት ፤ አስኪ እንዴው አንድ ቀን አማራ ተበደለ ብላችሁ ተናግራችሁ ታውቃላችሁ? አማራ በየቦታው እንዲህ ሲገፋ ለምን መናገር አቃታችሁ?

#እዘዝ ዋሴ፦

(ግለሰቡ ከሁሉም በፊት በረከትን በመወረፍ አዳራሹን ያነቃነቀ ሰው ነው።ግለሰቡ ከወደ በጌምድር አካባቢ ነው።በረከትን “አማራውን አንገቱ ደፍቶ እንዲሄድ ስታሸማቅቁት የኖራችሁ እናንተ እንጅ አማራው ኩሩና ጀግና ህዝብ ነበር፤ አሁን ግን እድሜ ለእናንተ ስም እያወጣችሁ እያሰደባችሁ ይኸው በየቦታው ይዋረዳል፤ ይህ ሊቆም ይገባል ሲል ተናግሯል።የእዘዝ ንግግር ብዙ ቢሆንም ስሙ ሳይጠቀሰ በቀደም በስፋት ስለፃፍኩት ብዙም አልልም።

አሁን ደግሞ በተቃራኒ ቡድን ከተሰለፉት ውስጥ ሌሎቹን ስለምታውቋቸው የትናንቱን አንድ ሰው ብቻ ላንሳ

#ዝማም አሰፋ፦

(ልክ የ2008 ዓ.ም የብናልፍ አቋምን በድጋሚ ያሳየች አሳፋሪ ሰው ሁናለች) ( ጎንደር ላይ ተወልዶ ሰው የፈራ እንድሆን ፣ እናቱን ጠይቋት ሽል ቀይራ እንድሆን፤ ይላል የጎንደር ሰው)፡፡ ዝማም የጎንደር የሰው በመሆኗ፤ሁሉንም አማራ ቢያሳፍርም ስራዋና ንግረሯ ግን፤ በተለይም ጎንደሬዎችን ክፉኛ ሀፍረት እንደተሰማቸው ማወቅ ችለናል፡፡ለነገሩ ዘግየት ብሎ እንደደረሰን መረጃ ሻንበል ከበደንና ቹቹ አለባቸውን ክፉኛ ስታስጠቃ የኖረችና ከኃላፊነት እንዲነሱም፤ከአለምነው ጋር ሁና ትልቁን ድርሻ እንደተወጣችም ሰምተናል፡፡በወቅቱ ሳይገባው ተስፋየ ጌታቸውም በስሱ ደግፏት ነበር ተብሏል። ለሴትዮዋ የህውሀት ነገር ደግሞ ሞቷነው፡፡ እስኪ በሞቴ መረጃ ያላችሁ ሰዎች አንዲት ነገር አጣርታችሁ ላኩልኝ፤ ዝማም በ1983 ዓ.ም ጎንደር ከተማ የኢህዴን ካድሬ ሁና ስትሰለጥን አሰልጣኝዋ አወጣ ገብሩ የሚባል የህውሀት ካድሬ ነበር አሉ፡፡ የዚህን ሰውየና የዝማምን ዝምድና ታውቃላችሁ? እንዴው ለህውሀት ይህንን ያክል የምትዋደቀው ከሀውሀተቶች ጋር ዝምድና/ ወዳጅነት ካለት ብየ ነው፡፡ እንግዲያ ምን እንበል፤ወገኗን አስጠልቶ እንዲህ ህውሀትን ያስወደዳት፡፡በእርግጥ በአወጣ ትግሬነት እርግጠኛ አይደለውም።እንዴው የዝማም ጉዳይ ቢጨንቀኝ እንጅ።ከቶ ምን አስነክተዋት ነው?ለዚያውም ዶ/ር አንባቸውን ለምስደብ የሞከረችው? የባለፈው ግን አይባቃትም?

ለሁሉም ወደ ዝማም የውሎዋ ንግግር ልውሰዳችሁ፡፡ ይች ባንዳ እድሉን እንዳገኘች፤የመጀመሪያ ስራዋ ያደረገችው፤ ጀግኖቹን ዶ/ር አንባቸው መኮነንና ፀጋ አራጌን መዝለፍ ነበር፡፡ ደ/ር አንባቸውና ጸጋ አራጌ ደግሞ ያደረጉትን ታሪካዊ ንግግር ከላይ አንስቸዋለሁ፡፡ በተለይ ፀጋ አራጌን እንዲህ አለችው፤ ፀጋ ይህ ችግር ሁሉ አለ ካልክ፤ ነባሮቹን ሰዎች (ሽማግሌዎቹን) ከመወረፍና ችግሩን ወደ ነሱ ከመግፋት ይልቅ፤እራስክን ለምን አታይም፤ ወልድያን ያቃጠልከው አንተ እኮነህ ብላ ሽማግሌዎቹን ለመከላከል ሞከረች እላችኃለሁ፡፡ አይ በሽታ፡፡

ዶ/ር አንባቸው እንደገና መድረኩን ወሰደና ዝማምን ጥባ ጥቤ ተጫወተባት ፤ እንዲህም አላት፤ አንች ሴት ከዚህም ከዛም እያንሸኳሸኩሽ ( ነገር ወዲህና ወዲያ እያወሰድሽና እያመጣሽ)፤ ስታባይን የኖርሽ አንች ነሽ፤ብሎ ቀልቧን ገፈፈው፡፡በ2008 ዓ.ም ወጣቶች የረገፉብን በማን ሆነና? መረጃ ኑሮን ለቅሶ እንኳን እንዳንደርስ ስልክ ሳይቀር የተዘጋብን እናንተ በምታደርጉት የውስጥ መረጃ ልውውጥ አይደለምን? በማለት በስሜት ብዙ ነገር ተናገረ።

የተሳታፊው ሁኔታ፤

በዚህ መድረክ እንደታዘብነው፤ ሰው አምሯል፤ የአማራ ብሄርተኝነት ላይቀለበስ ተቀጣጥሏል፤ በብአዴን ጥረት ሳይሆን በህዝባችን ግፊት ቢሆንም የአማራ ታሪክ መታደሻው ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ማሳያው ከላይ የተናገሩት ሰዎች ሁሉም የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን ስናይ ተስፋችን ትልቅ መሆኑን እንረዳለን፡፡ አማራን ነጻ በማውጣት ዛሬም አማራን ለህውሀት ተገዥ አድርጎ ለመቀጠል በሚፈልጉየለውጥና አድሀሪ ኃይሎች መካከል ትግሉ ተጠናክሯል፡፡ ትልቁ ተስፋ ደግሞ መድረኩን እንደታዘብነው፤ አብዛኛው የኮንፈረንስ ተሳታፊ የለውጥ ኃይሉን ደግፎ የቆመ መሆኑነው፡፡ ይህ ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ እነበረከትና ቡድኑ የህውሀትነን ተልዕኮ በአማራ ምድር ለማስፈጸም ወደማይችሉበት ደረጃ እየቀረቡ ይመስላል፡፡መረሳት የሌለበት ግን የብአዴን ገመድ ተሰፍሮ የተሰጠው እንጅ ያለገደብ አለመሆኑ ነው።ያም ሁኖ አሁንም እነሱን ግባ ከምድር ሳናወርድ መዘናጋት የለም፡፡ ትግሉ ገና ነው፤ አማራን ማንም የመንደር ወንደበሬ ከምድር እየተነሳ መደል ይቅርና ስሙን በክፉ መጥራት እማይችልበት ደረጃ መድረሱን ማረጋገጥ አለብን፡፡

የሚጠበቀው የዛሬ ውሎ፤

በእቅዱ መሰረት ዛሬ ጥዋት ሲገባ፤ የመናገር እድሉን መድረክ መሪዎቹ በመውሰድ የግላቸውንና እንደ መሪ የሚሉት ይኖራል ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን በረከትና ቡድኑ ሃሳብ አለን ስላሉ፤ውይይቱ በታሰበው መልኩ እንደማይጀመር ፍርሀት አለ፡፡ ለእነ በረከት ቡድን እድል ከተሰጠ፤ እጁን እንደ ጭራሮ አቁሞ ዛሬ እድል የተነፈገው ካድሬ እኛም እድል ይሰጠን ብሎ አጸፋ መመለሱ እንደማይቀር ይጠበቃል፡፡ ይህም መድረኩ እንደገና ሊራዘም ይችላል፡፡
መድረክ መሪዎቹ አራቱ ናቸው፡፡ ደመቀ፤ገዱ፤ጌታቸው እና አለምነው፡፡

አንዱ ኮሚክ እንዲህ ይለኛል፦

<<ደመቀ ነገሩን አድበስብሶና የአስታራቂነት ሚና ተጫውቶ ለማለፍ እንደሚሞክር ተገምቷል፤ ገዱና ጌታቸው ደግሞ እንቅጭ እንቅጩን ይነጋራሉ ተብለው እየተጠበቁ ነው፡፡ተስፋየም እንዲሁ። የአለምነው ነገር ቸግሯል፤ ስለ አለምነው እኔን ጨነቀኝ፡፡አስከሬን ጠባቂ እንዴት አያስጨንቅም ትላላችሁ ጎበዝ? አውጭ ወይም ጅብ ቢበላውስ? አለምነው ምን ሊል ይሆን? ከነበረከት ጎን እንዳይቆም ድሮም በህዝብና በካድሬው የተጠላ ነውና አሁን ከነበረከት ጎን በመሰለፍ መጠላቱን ዳብል ሊያደርገው ነው፤ ከነገዱ ወገን እንዳይሆን ደግሞ ሽንፈት ሊሆንበት ነው፤ ምክንያቱም ሲልና ሲሰራ የኖረውን ያውቀዋላ፡፡ እናንተየ ግራ ተጋባን ፤ አይ አለምነው አንተም እንዲህ ተቸግረህ እኛንም እንዲህ ታስጨንቀን? ይብላኝልህ ክፉ ሰው ነህ፡፡>>

ማጠቃለያ/ ከዝግጅት ክፍሉ መልዕክት

ትግሉ ተናክሮ ቀጥሏል፡፡ አማራ ነጻ መውጫው ጊዜም እየተቃረበ ነው፡፡ ግን አሁንም ፈተና አለ፡፡ በብአዴን ውስጥ ያለው አሰላለፍ አሁን መልክ ቢይዝም እነዚህ ሽንኮፎች በብአዴን ውስጥ እስካሉ ድረስ መዘናጋት አይገባም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የአማራ ህዝብ እያስጠቁ ያሉ ባንዳዎች ከአማራ ምድርና ስርአተ መንግስቱ እስካልተወገዱ ድረስ ህውሀት ዛሬም የህልውና ስጋታችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፤ ህውሀት አማራን ያጠቃው በቀጥታ ሳይሆን በአብዛኛው ብአዴን ውስጥ ባሉ ተላላኪዎቹ ነው፤ አሁን እነዚህ ተላላኪዎች በደንብ ታውቀዋል፤ ቀሪው ስራ ባካችሁ ልቀቁን ብሎ ማሰናበት ነው፤ሰለቻችሁን ፤ተውን ማለት ነው፡፡

አሁን በብአዴን ኮንፈረንስ ተሳታፊ የሆናችሁ የአማራ ልጆች ሆይ ፤ ብዙዎቻችሁ የወገናችሁ መበደል እንደገባችሁ፤ አስጠቂዎቹም እነማን እንደሆኑ እንደተገነዘባችሁት አውቀናል፤ጥሩ ጅምርም እያሳያችሁ ነው፡፡ በዚህ ኮንፈረንስ ከላይ የተዘረዘሩትን ባንዳዎች እንዲሆም ሌሎች ከዚህ በፊት የምታውቋቸውን ካላሰናበታችሁ ታጥቦ ጭቃ መሆኑን አትዘንጉ፤ እነሱን ከብአዴን ሳታባሩ ሄዳችሁ ማለት፤ታሪካዊ ስህተት ሰራችሁ ፤እንዲሁም የአማራ ህዝብ ችግር እንዲቀጥል ፈቀዳችሁ ማለት ነው፡፡

አሁን ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም፤ ተውን ማለት ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ይሄን እድል ተጠቀሙበት፤ ጥሩ አጋጣሚ ገጥሟችኃል፡፡ ታሪካዊ ስህተት በመስራት የህዝባችሁን ችግር እንዳታራዝሙ፤ አደራ …አደራ…..
የነገውን ውሎ ደግሞ፤ አደራጅተንና ቀሪ ሃሳቦችን ጨምረን እንመለሳለን፡፡

በልጆቹ መስዋትነት አማራ ታሪኩን ያድሳል !

(የአለምነው መኮነን በተስፋየ ጌታቸው ተተክቷል)

<<በረከት ከሀዲ ነው>>ከሰዓት በፊት የነበረው ውይይት

ይህንን መልዕክት የመልዕክት መቀበያየን ስፈትሽ ጠዋት ተልኮልኝ ሳላየው ቀርቸ አሁን ያገኘውት እና ላካፍላችሁ የወደድኩት ነው።በይት ከላይናው ባይለይም ታነቡት ዘንድ ልጋብዛችሁ።

በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የብአዴን በጥለቀት የመበስበስ ኮንፈረንስ በዛሬዉ እለት ለየት ያለ፣ተለምዶ፣ተነግሮና ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ንትረኩ አይሎ ዉሏል፡፡

ንትረኩ የተጀመረዉ በትናንትናዉ እለት የህወሃቱ በረከት ስሞኦን የሰጠዉን ሀሳብ ተከትሎ ሲሆን ከወረዳና ከዞን የመጣዉ አመራር ብቻ ሳይሆን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ጭምር በረከትንና ወልቃይትን የሸጠዉ ተላላኪዉ አዲሱ ለገሰን እንዳይነሱ አድርገዉ እንደ እባብ ቀጥቅጠዋቸዋል፡፡መነሻ ምክንያቱ ትናንት የሰጠዉን ሃሳብ ተከትሎና ዶ/ር አብይ አህመድ ለጠ/ሚ ሲመረጥ በቡድነኝነትና በአደረጃጀት በተፈጠረ ጋብቻ ነዉ፣አመራሩ ብቃት የለዉም፣ብአዴን እየተመራ አይደለም፣ሀገሪቱም እኛን አልቦ ዋጋ የላትም ወዘተ የመሳሰሉትን ሀሳቦች አንስተዉና በኢህአዴግ ደረጃ የተወያዩትን እንደወረደ ማቅረብ ችግር ስለሚፈጥር በጥንቃቂ እንዲመራ ለሁሉም ብሄራዊ ድረጅቶች የተነገራቸዉን በረከትና አዲሱ አፍርሰዉ የተመረጠዉን ጠ/ሚ ጭምር በማጣጣላቸዉና የተቀበሉ አለመሆኑን ለኮንፈረሰኛዉ በማቅረባቸዉ የተነሳ በዛሬዉ እለት በዶ/ር አንባቸዉ ሂሳባቸዉ ተወራርዶላቸዋል፡፡

ዶ/ሩ ያነሳቸዉ፡- እኔ መሞት ካለብኝ ዛሬ መሞት አለብኝ በረከት ከሃዲ ነዉ፡፡ ድረጅቱን ክዶ ሚስጥር አልጠበቀም ስለዚህ በደንብ መነጋገር አለብን በማለት ነዉ የጀመረዉ፡፡

 በረከት የብአዴን ታጋይ ተሸማቆ እንዲኖር ያደረገ ሰው ነዉ
 የህዝባችን መሰረታዊ ጥያቂወችን ስናነሳ ትምክት፣የድሮ ስረዓት ናፋቂ፣ደርግ እያለ አንገታችን አስደፍቶናል፣አዋርዶናል፣
 በረከት ደረግ እያለ እያሸማቀቀ ነገር ግን እህአዴግ ከደርግ የበለጠ ገዳይ ሆኖ አልቆየም ወይ;
 ያን ሁሉ ወጣት አስጨፍጭፈን ዝም እንዴት እንላለን፣እስቲ የህዝቤን መሬት ለማዳመጥ በተለይም ልወጇየሞተባትን እናት ስሜት ለማዳመጥ እስቲ የራሳችን ልጅ እያኝዳንዳችን እንግደልና እንየዉ፣ምን ያህል እንደሚዘገንንና ህዝቡን እንዴት አንደበደልነዉ እንየዉ፡፡ በረከት የዚህ ሁሉ ባለቤት ነህ የደባርቅ ህዝብ ገደሉን ድረሱልን ሲለን እኮ አቅም ስለለለን ዝም ብለን ሲያልቁ አይተናል፡፡ በስልካችን እንኳን መነጋገር እንዳንችል ስልካችን እየተጠለፈ ነጻነታችን ተነፍገን ሽባ እንድንሆን ተደርገናል፡፡ የአማራን ሀብትና ንብረት ባንተና ባዲሱ ትዛዝና ጉዳይ አስፈጻሚነት አንደፈለጉ ሲናኙበት እንዲኖሩ አድርገሃል፡፡ አንተ ያልከዉ ሃሳብ ካልተደመጠ ርምጃ ታስወሰዳለህ፡፡

በአደረጃጀት ከግሙ የብአዴን ጠላት ሆኖ ከህወሃት ጎን ተሰልፎ ሲያስገድል ከቆየዉ ኃ/ማሪያም ወደ ሽፈራዉ ሽጉጤ ስልጣን ለመስጠት ስትለፋና ስታደራጅ አልቆየህም ወይ

 ለምን ለቀቅ አታደርጉንም፣እስቲ ዳር ሁኑና አዲሱን አመራር እዩት፣
 የአማራ ህዝብ መሮታል ተዉን ከዚህ በኃላ ላንመለስ አታሸማቁን ተቆጥተናል በደሮ ንግግራችዉና ቃላቶቻችሁ እንሸማቀቅም ጥላቸዉን ዉጡ፣

 የአማራ ህዝብ አለማም እዉነቱን እንነጋገር፣ እስቲ እንቁጠር እናነጻጽር የሚል ሀሳብ እየሰጠ እንዳለ የመሳ ሰዓት በመድረሱ ከሰዓት ሊቀጥል ጠበትኗል።