የሰፈርና የአእምሮአችንን ቆሻሻ እያጸዳን በንጹሕ ልቦና እና አእምሮ ሀገራችንን እናድስ ፤ሀገራች እንገንባ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልእክት አስተላለፉ

˝የሰፈርና የአእምሮአችንን ቆሻሻ እያጸዳን በንጹሕ ልቦና እና አእምሮ ሀገራችንን እናድስ ፤ሀገራች እንገንባ ˝ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልእክት አስተላለፉ።

ጥሪ በተደረገው መሠረት በመላዉ ኢትዮጵያ ጠዋት ጽዳት ሲደረግ ቆይቷል።
አብዛኛዉ ቦታ ላይ ያለው እንቅስቃሴ የሠመረ ነው።

˝የሰፈርና የአእምሮአችንን ቆሻሻ እያጸዳን በንጹሕ ልቡና እና አእምሮ ሀገራችንን እናድስ ፤ሀገራችንን እንገንባ። ˝

ለቀጣይነቱ እንደ ባሕል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እንድትቀጥሉበት እጠይቃለሁ ብለዋል።
ዛሬ መውጣት ያልቻላችሁ ከዚህ ትምህርት ወስዳችሁ ኃላፊነታችሁን እንደምትወጡና ባሕል እስኪሆን ድረስ እንደምታስቀጥሉት አምናለሁ ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው በጽዳት ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነዋል::

ምንጭ፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE