የቀድሞ የደሕንነት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አሰፋ በሌሉበት ሊከሰሱ ነው!

አቶ ጌታቸው አሰፋ በሌሉበት ሊከሰሱ ነው! በአገር ውስጥ ተቀምጠው በሌሉበት መከሰሳቸው አነጋጋሪ ሆኗል!

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃ እና ደህነንት መሥሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር የነበሩትና ለዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሞት ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ፤ በሚቀጥለው ሳምንት በሌሉበት ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ …

በህግ የሚፈለጉት አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ የትግራይ ክልላዊ መንግስት የጸጥታ ሃላፊ ሆነው መሾማቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቢቆይም፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋ አልተሾሙም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

አቶ ጌታቸው በወቅቱ የት እንደሚገኙ የተጠየቁት ዶ/ር ደብረጽዮን፤ ”ተደብቀዋል” ማለታቸው አይዘነጋም:: ጠቅላይ አቃቤ ህግ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋን ለህግ ለማቅረብ የክልሉ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ለሁለተኛ ጊዜ መጠየቃቸውን ለማወቅ ባይቻልም፣ በሌሉበት ክስ ይመሰረትባቸዋል ተብሏል፤ የክሱ ይዘት በትክክል አልታወቀም፡፡

ምንጮች እንደሚሉት፤ ከጠ/ሚኒስትሩ የግድያ ሙከራ፣ በእስረኞች ላይ ከሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ከሙስና ጋር የተያያዙ ክሶች ሊመሰረትባቸው ይችላል፡፡

ምንጭ፦ አዲስአድማስ