በወሎ ዩኒቨርስቲ የተቋረጠው ትምህርት የፊታችን ሰኞ ይጀመራል ተባለ

በወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል እርቅ ወረደ ከቀናት በፊት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት መፈታቱን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎችና ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

ባለፈው ማክሰኞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው በተቀሰቀሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንና ሌሎች መጠነኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ህክምና ተሰጥቷቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን ለዶየቼ ቬለ DW ተናግረዋል፡፡

በተማሪዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የዞን ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተማሪ ተወካዮች ባደረጉት ጥረት ችግሩ መፈታቱንም አስታውቀዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሀኑ አሰፋ እርቅ መፈፀሙን አረጋግጠው የተቋረጠው ትምህርት የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር አመልክተዋል፡፡

የተማሪዎቹ ተወካዮች የሀይማኖት አባቶችና ሌሎችም የመንግስት አመራሮችና ተማሪዎች ባደረጉት ጥረት ሰላም መውረዱን መናገራቸውን DW ዘግቧል፡፡ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚያስተምራቸው ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች አሉት፡፡