የለውጡ ቀጣይነት አሳሳቢ ነው – ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ልዩ ልዩ መብቶች እየተከበሩ ቢሆንም የለውጡ ቀጣይነት ግን እንደሚያሳስበው አስታወቀ።ድርጅቱ ካለፈው ሳምንት አንስቶ በ8 ርዕሶች በተከታታይ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት እና ሌሎች መሰል መብቶች እየተከበሩ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እና በድርጅቱ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከፍተኛ ተመራማሪ ፌሊክስ ሆርን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተባባሰው ግጭት ምክንያት የለውጡ ቀጣይነት እንደሚያሳስብ ተናግረዋል። መንግሥት ግልጽ እቅድ በማውጣትም ህግ እና ስርዓትን ሊያስከብር እንደሚገባም አሳስበዋል።  ዝርዝሩን …….. ያዳምጡት


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE