የዶክተር ዐቢይ የአንድ ዓመት አስተዳደር በHRW ግምገማ

ድርጅቱ በ8 ርዕሶች ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት እና ሌሎች መሰል መብቶች እየተከበሩ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እና በድርጅቱ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከፍተኛ ተመራማሪ ፌሊክስ ሆርን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተባባሰው ግጭት ምክንያት የለውጡ ቀጣይነት እንደሚያሳስብ ተናግረዋል።…