በኬንያ እየጨመረ የመጣው የመንግሥት ተቃዋሚዎች ታፍኖ መሰወር እጅግ እንዳሳሰባቸው የመብት ቡድኖች፣ የሕግ ባለሙያዎችና ፖለቲከኞች በመግለጽ ላይ ናቸው።
ቢሊ ምዋንጊ የተባለ የ24 ዓመት ወጣት ባለፈው ሳምንት በተሰወረባት ኢምቡ በተሰኘች ከተማ ተቃውሞ ተካሂዷል።
ባለፈው ሰኔ እና ሐምሌ በፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት ላይ በአብዛኛው በወጣቶች የተመራ ተቃውሞ ከተደረገ ወዲህ፣ የሃገሪቱ የፀጥ…