አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ላደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስቶ ነበር።
ድርጅቱ፣ ፕሬዝዳንት ማክሮን የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች በአማራና ኦሮሚያ ክልል እየፈጸሙት ይገኛሉ ያለውን “የጦር ወንጀል” እንዲያቆሙ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ትዕዛዝ እንዲሠጡ ለማሳመን ይሞክሩ እንደኾነ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ባሠፈረው መልዕክት ጠይቋል።
ድርጅቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችና የተጠያቂነት መጥፋት ባስቸኳይ እንዲያበቃና የሲቪል ማኅበራት በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ መደረግ እንዳለበትም አሳስቧል።