በዘመቻ መቶ ተራሮች የተማረኩ ምርኮኞች በድሮን ተጨፈጨፉ !
ከወራት በፊት በአማራ ፋኖ በጎጃም 3 ኛ ክ/ጦር የተማረኩ መርኮኞች በጊዜያዊነት ፋግታ አካባቢ በካምፕ የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ቀይ መስቀል እንዲረከባቸው ለማድረግ እየተሰራ እንዳለ ምርኮኞቹን አግኝቼ የተወሰኑትን አናግሬያቸው ነበር።
አንደኛው ምርኮኛ ጋር ስንነጋገር “ወንድም ከሞት ተረፍን ብለን ተደስተን ሳንጨርስ ወደሞት አትውሰዱን ” አለኝ ።
አልገባኝም ነበርና ምነው ምን ሰምተህ ነው ስለው።
የውልህ ከ2ዓመት በፊት በትግራዩ ጦርነት ተካፍየ በትግራይ ኃይሎች ከ10,000 በላይ ሆነን ተማርከን ለቀይ መስቀል አሳልፈው ሰጡን ቀይመስቀልም ለመከላለያ አሳልፎ ሰጠን ዞረን ከአማራ ጋር ጦርነት ማገዱን አሁንም እናንተ ለቀይመስቀል ከሰጣችሁን ከመግደል አይተናነስምና አትግደሉን ነበር ያለኝ።
ዛሬ ፋግታ ላይ ካምፕ ውስጥ እንዳሉ በድሮን ጥቃቱ ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል። (ፋኖ ጥላሁን አበጀ )