ጦሯ በቅርቡ ከሶማሊያ እንደሚወጣ ቢጠበቅም፣ ኢትዮጵያ አልሻባብን መዋጋቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ “በየትኛውም ሁኔታ አልሻባብን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት፣ ራሷን ነጻ አገር አድርጋ ከምትቆጥረው ከሶማሊላንድ ጋራ…