የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊና ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኙትን ከየክልሎቹ የተፈናቀሉ ዜጎችን ቁጥር መሰረት በማድረግ የገንዘብ ድጋፉ ክፍፍል መካሄዱን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ለሶማሌ ክልል 35 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር፣ ለኦሮሚያ ክልል 33 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር፣ ለደቡብ ክልል 18 ሚሊዮን ብር እና ለአማራ ክልል 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ነው ያስታወቀው፡፡

ባንኩ ለትግራይ ክልል 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር፣ ለቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር፣ ለጋምቤላ ክልል 454 ሺህ ብር፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 387 ሺህ ብር እና ለሀረሬ ክልል ደግሞ 62 ሺህ ብር ነው ድጋፍ ያደረገው ብሏል ኤፍ ቢ ሲ በዘገባው።