በጅግጅጋ ሄጎ በተባሉ የተደራጁ ወጣቶች ጥቃት የደረሰባቸውን ዜጎች የሱማሌ ክልል ሊያቋቁማቸው ነው

በሱማሌ ክልል ሄጎ በተባሉ የተደራጁ ወጣቶች ጥቃት የደረሰባቸውን ዜጎች የክልሉ መንግስት ሊያቋቁማቸው ነው ።ሄጎ በተባለ የወጣቶች አደረጃጀት አማካኝነት ከ4 ሺ በላይ ግለሰቦች ልዩ ልዩ ጥቃቶች ተፈፅሞባቸዋል፡፡የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች ጥቃት የተፈፀመባቸውን የክልሉን ልዩ ልዩ ብሔረሰብ ነዋሪዎች ለማቋቋም 100 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታወቀ፡፡ አሁን የሚደረገው ድጋፍም የፈረሱ ቤቶችን ለመጠገንና የወደሙ ንግዶችን መልሶ ለማቋቋም ይውላል