የትኛውን ሰንደቅ አላማ ነው የምታከብሩት?

የትኛውን ሰንደቅ አላማ ነው የምታከብሩት?
አገዛዙ “የሰንደቅ አላማ ቀንን እያከበርኩ ነው” እያለ እየቀለደ ነው። ግን ምን እንደሚያከብር እንኳን አያውቅም!
አረንጓዴ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ቀለሞቹን ስታዩ የሚያስደነግጣችሁን ሰንደቅ አላማ ነው እውነት የምታከብሩት?
ቀለሞቹን ልብስ ላይ ስታዩዋቸው ነጠላ ስትቀዱ የከረማችሁትን ነው የምታከብሩት? የህፃናትና አዛውንቶች አንገት ቀምታችሁ የቀደዳችሁትን ታከብራላችሁ?
ቀለማቱን የእጅ ማጌጫ፣ የቁልፍ መያዥያ ወዘተ ላይ ስታዩ ሰብስባችሁ ያቃጠላችሁትን ሰንደቅ አላማ ነው የምታከብሩት?
ፍተሻ ጣቢያ ላይ ቀለማቱ የታተሙባቸውን ቁሶች እየቀማችሁ የጣላችሁትን፤ ህዝብ ያንገላታችሁበትን፣ መንገድ ላይ ሰው ነጥላችሁ ያሰራችሁበትን ቀለም ነው የምታከብሩት?
የሰንደቁን ቀለሞች ያደረገ ኦርቶዶክስ፣ አማራ ወዘተ እያላችሁ ለይታችሁ ማጥቂያ ያደረጋችሁበትን ቀለሞች ውጤት የሆነውን ሰንደቅ አላማ እያከበራችሁ ነው?
የክልል ባንዲራ ላዩ ላይ የምታንጠለጥሉበትን፣ በዓል ሲኖር ከከተማው ሙልጭ አድረረጋችሁ የምታነሱትን ሰንደቅ አላማ እያከበራችሁ ነው?
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለምን ትጠሉታላችሁ እንጅ ታከብሩታላችሁ? ማሳደጃ፣ ማጥቂያ፣ ለይቶ መምቻችሁን እናከብረዋለን እያላችሁ ነው? መንገድ ላይ ቀምታችሁ የምትረግጡትን እንዴት ታከብሩታላችሁ?
በርካታ አገራት ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀለም ሲወስዱ እናንተ ከኢትዮጵያ ተፀይፋችሁ ከሌላ አገር የሰንደቅ አላማ ቀለም ወስዳችሁ እንዴት እንደምትጠሉት በተግባር ያሳያችሁትን ሰንደቅ አላማ ነው ቀን ቆርጣችሁ የምታከብሩት?
በሰንደቅ አላማው ቀለም ምክንያት የተንገላቱ፣ ተለይተው የተጠቁ፣ ነውሩን በአካልና በሚዲያ ሲመለከቱ የከረሙ፣ ያሸማቀቃችኋቸው ኢትዮጵያውያን እንኳን የሚታዘቡ፣ የሚያገናዝቡ አይመስላችሁም?