የታቀደው ዘመቻ አማራውን አስርበን እናሸንፈዋለን የሚል ነው።

የታቀደው ዘመቻ አማራውን አስርበን እናሸንፈዋለን የሚል ነው።
ብልፅግና በካድሬ እስር እንደጀመረው ተደርጎ የሚያስነግረው ዘመቻ ቀጣይ ኢላማ ህዝብ ነው። “እነሱንስ ይበላቸው” ተብሎ ወደ ህዝብ ነው ዋናው ዘመቻ። የመኸር ወቅት ነው። በእርግጥ ካድሬውንም ባያምነው ዋናው ኢላማ ግን ህዝብ ነው። በይፋ ፋኖን ህዝብ ደግፎታል ብለው ገምግመዋል።
አሁን አሳውን ለመያዝ ባህሩን ማድረቅ አለብን የሚል ዘመቻ ነው የቀጠለው። መረጃ ይሰጣሉ ያሏቸውንም ሌላውንም ካድሬ አስረው የፋኖ ደጋፊ ተብሎ የተፈረጀን ህዝብ ግን መመታት አለበት ብለው ወስነዋል። እስካሁን ቤት ለቤትም ሆነ መንገድ ላይ ሲገድሉት የከረሙት አማራ ላይ ነው ዘመቻው። ደግሞ በዚህ የመኸር ወቅት።
ወቅቱም የተመረጠበት አማራው ምርቱን ሳይሰበስብ ወደ ጦርነት ማስገባት፣ ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል ነው። በዚህ ሂደት አመት የለፉበት መና ይቀራል የሚል ጠላትነት ነው። የተፈጥሮ አደጋና ጦርነት ሲፈራረቅበት የከረመ ህዝብ ለርሃብ ይዳረጋል። እርዳታ የሚሰበስበው ደግሞ አገዛዙ ነው።
አማራውን ያዘመረውን እንዳይሰበስብ አድርጎ የእርዳታ እስረኛ ማድረግና ማሸነፍ ነው። ጦርነቱ ህዝብ ላይ ከከረመው የባሰ ቀውስ እንዲያመጣ ነው ዕቅዱ።
ነገር ግን ህዝብን በዚህ መንገድ ማሸነፍ አይቻልም። ከአሁን ቀደምም በርካታ የጥላቻ ዘመቻዎች ተደርገው ውጤታቸው ታይቷል።