በሱማሌ ክልል በአንድ መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሃን ተገደሉ

በሱማሌ ክልል በአንድ መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሃን ተገደሉ

በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዋርዴር ከተማ በአንድ መስጂድ ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የአገር ሽማግሌ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ.ም. በምሥራቃዊ የክልሉ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ዶሎ ዞን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ፤ በአካባቢው ባሉ ጎሳዎች መካከል ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረ ግጭት ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ተነግሯል።