ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ኢትዮጵያን የሚደፍር አስር ጊዜ ማሰብ ይኖርበታል” አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትኛውም አገር “ኢትዮጵያ መድፈር ሲፈልግ አንዴ ሳይሆን አስር ጊዜ ማሰብ ይኖርበታል” ሲሉ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ጳጉሜ 3/2016 ዓ.ም. በተከበረው “የሉዓላዊነት ቀን” ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላም እና መረጋጋት መሆኑን ገልጸው ይህን አልፈው የሚመጡ ኃይሎችን ግን አገራቸው እንደምትከላከል ተናግረዋል።