በናይጄሪያ ነዳጅ ጫኝ ቦቴ ከሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ቢያንስ 48 ሰዎች ሞቱ

ናይጄሪያ ማዕከላዊ ግዛት ኒጀር አንድ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ሰዎች እና የቁም እንስሳትን ከጫነ መኪና ጋር ተጋጭቶ በተቀሰቀሰ እሳት ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኤጀንሲ ገልጿል።
ኤጀንሲው ይህ አደጋ ያጋጠመው ትላነት ዕሁድ እንደነበር ገልጾ ሁለቱ ተሽከርካሪዎች ሲጋጩ ከፍተኛ ፍንዳታ ተከስቶ እንደነበር ጠቅሷል። በዚህም ሳቢያ ተሽከርካሪዎቹ በከፍተኛ እሳት መዋጣቸ…